የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwfq ርዕስ 33
  • የይሖዋ ምሥክሮች ፕሮቴስታንቶች ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የይሖዋ ምሥክሮች ፕሮቴስታንቶች ናቸው?
  • ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የይሖዋ ምሥክሮች የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታዮች ናቸው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ክፍል 17:- ከ1530 እዘአ ወዲህ የፕሮቴስታንቶች እንቅስቃሴ በእርግጥ ተሐድሶ ነበርን?
    ንቁ!—1996
  • የላቲን አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በጭንቅ ላይ ትገኛለች በሚልዮን የሚቆጠሩት አባሎቿ ትተዋት የሚወጡት ለምንድን ነው?
    መጠበቂያ ግንብ—1993
  • ውሳኔ ለማድረግ ጊዜው አሁን የሆነው ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
ijwfq ርዕስ 33
አንድ የይሖዋ ምሥክር ለአንድ ሰው ስለ እምነቱ ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ሲያስረዳ

የይሖዋ ምሥክሮች ፕሮቴስታንቶች ናቸው?

አይደሉም። የይሖዋ ምሥክሮች ክርስቲያኖች ናቸው፤ ያም ቢሆን ፕሮቴስታንቶች አይደለንም። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው?

ፕሮቴስታንት ለሚለው ቃል “የሮም ካቶሊክን የሚቃወም” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። እርግጥ ነው፣ የይሖዋ ምሥክሮች የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የምታስተምረውን ትምህርት አይደግፉም፤ ያም ቢሆን በሚከተሉት ምክንያቶች የተነሳ ፕሮቴስታንት አይደለንም፦

  1. በርካታ የፕሮቴስታንት ትምህርቶች ከትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር ይጋጫሉ። ለምሳሌ ያህል፣ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው “አንድ አምላክ” እንዳለ ነው፤ በመሆኑም የሥላሴ ትምህርት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ የለውም። (1 ጢሞቴዎስ 2:5፤ ዮሐንስ 14:28) በተጨማሪም አምላክ ክፉዎችን የሚቀጣው በገሃነመ እሳት በማቃጠል ሳይሆን ለዘላለም ከሕልውና ውጭ እንዲሆኑ በማድረግ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ ይናገራል።—መዝሙር 37:9፤ 2 ተሰሎንቄ 1:9

  2. የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ሌላ ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ቡድን አንቃወምም ወይም ሃይማኖቱን ለማሻሻል አንሞክርም። በአንጻሩ የአምላክን መንግሥት ምሥራች በመስበክ ሰዎች በምሥራቹ ላይ እምነት እንዲኖራቸው ለማድረግ እንሞክራለን። (ማቴዎስ 24:14፤ 28:19, 20) ዓላማችን ሌሎች ሃይማኖታዊ ቡድኖችን ማሻሻል ሳይሆን ፍላጎት ያላቸውን ሰዎች ስለ አምላክና ስለ ቃሉ መጽሐፍ ቅዱስ እውነቱን ማስተማር ነው።—ቆላስይስ 1:9, 10፤ 2 ጢሞቴዎስ 2:24, 25

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ