የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 64
  • ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራት ይኖርብኝ ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራት ይኖርብኝ ይሆን?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቡድን መፍጠር ምን ጉዳት አለው?
  • ምን ማድረግ ትችላለህ?
  • ጥሩ ጓደኞች—መጥፎ ጓደኞች
    ንቁ!—2005
  • ጓደኞችህን በጥበብ ምረጥ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ጥሩ ጓደኞች እንዲኖሩኝ ምን ላድርግ?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
  • የተሻሉ ጓደኞች ያስፈልጉኝ ይሆን?
    ንቁ!—2009
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 64
በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሴቶች ራሳቸውን ፎቶ ለማንሳት ቆመው

የወጣቶች ጥያቄ

ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራት ይኖርብኝ ይሆን?

“በጣም ከምቀርባቸው ልጆች ጋር ስሆን ነፃነት ይሰማኛል፤ ከዚያ ውጭ ካሉ ሰዎች ጋር መሆን ለእኔ በጣም ከባድ ነው።”—አለን

“በጣም የምቀርባቸው ጥቂት ጓደኞች አሉኝ፤ ከዚህ የበለጠ እንዲሰፋ አልፈልግም። ከብዙ ሰው ጋር መቀራረብና ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር ማውራት ይከብደኛል።”—ሳራ

አንተስ እንደ አለንና ሳራ ይሰማሃል? በጣም የምትቀርባቸው የተወሰኑ ጓደኞች ያሉህና ሌሎች ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራት የሚከብድህ ዓይነት ሰው ነህ?

ከሆነ ይህን ርዕስ በጣም ጠቃሚ ሆኖ ታገኘዋለህ!

  • ቡድን መፍጠር ምን ጉዳት አለው?

  • ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ቡድን መፍጠር ምን ጉዳት አለው?

በጣም የምትቀርባቸው ጓደኞች ያሉህ መሆኑ ምንም ስህተት የለውም። ከተወሰኑ ሰዎች ጋር የቅርብ ጓደኝነት መመሥረትህ ተፈላጊ እንደሆንክ እንዲሰማህ የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ እነዚህ ጓደኞችህ ከነድክመቶችህ ሊቀበሉህ ፈቃደኞች እንደሆኑ ታውቃለህ።

“በሌሎች መወደድና በአንድ ቡድን ውስጥ መታቀፍ ደስ የሚል ነገር ነው። ወጣት ስትሆን ደግሞ በሌሎች ዘንድ ተቀባይነት ማግኘት ትፈልጋለህ።”—ካረን፣ 19

ይህን ታውቅ ነበር? ኢየሱስ በርካታ ጓደኞች የነበሩት ሲሆን ከእነሱ መካከል 12ቱ ደቀ መዛሙርት ይገኙበታል፤ ከ12ቱ መካከል ደግሞ ይበልጥ ይቀራረብ የነበረው ከጴጥሮስ፣ ከያዕቆብ እና ከዮሐንስ ጋር ነበር።—ማርቆስ 9:2፤ ሉቃስ 8:51

ይሁንና ከተወሰኑ ልጆች ጋር ብቻ መቀራረብና ሌሎችን ማግለል ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። እንዲህ ማድረግ ከሚያስከትላቸው ጉዳቶች መካከል፦

  • ጥሩ ጓደኝነት ልትመሠርት የምትችልበትን አጋጣሚ ያሳጣሃል።

    “ከአንተ ጋር ከሚመሳሰሉ ሰዎች ጋር ብቻ ጓደኛ መሆንህ አዳዲስ ነገሮችን ማወቅ የምትችልበትንና ከሌሎች ጥሩ ሰዎች ጋር የምትተዋወቅበትን አጋጣሚ ይዘጋብሃል።”—ኤቫን፣ 21

  • ኩራተኛ ሊያስመስልህ ይችላል

    “ከተወሰኑ ሰዎች ጋር ብቻ የምትቀራረብ ከሆነ ከሌሎች ጋር ፈጽሞ መቀራረብ የማትፈልግ ሊያስመስልብህ ይችላል።”—ሳራ፣ 17

  • በጉልበተኝነት ድርጊት እንድትካፈል ሊያደርግህ ይችላል

    “አንተ የጉልበተኝነት ድርጊት አትፈጽም ይሆናል፤ የአንተ የቅርብ ጓደኞች እንደዚያ ሲያደርጉ ግን ምንም ላይመስልህ እንዲያውም ሊያስቅህ ይችላል።”—ጀምስ፣ 17

  • ችግር ውስጥ ሊከትህ ይችላል፤ በተለይ ደግሞ ምንም ይምጣ ምን ከዚያ ቡድን መለየት የማትፈልግ ከሆነ ለችግር ልትዳረግ ትችላለህ።

    “በጣም የሚቀራረቡ ጓደኞች ባሉበት ቡድን ውስጥ አንድ መጥፎ ሰው ካለ መላው ቡድን በተጽዕኖው ሊሸነፍና መጥፎ ድርጊት ወደመፈጸም ሊያመራ ይችላል።”—ማርቲና፣ 17

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • መሥፈርቶችህን መርምር

    የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን ጠይቅ፦ ‘ሕይወቴን ለመምራት ጥረት የማደርገው በየትኞቹ መሥፈርቶች ነው? ጓደኞቼ በእነዚህ መሥፈርቶች መመራት ቀላል እንዲሆንልኝ እያደረጉ ነው? ጓደኞቼን ላለማጣት ስል ማንኛውንም መሥዋዕትነት እከፍላለሁ?’

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “መጥፎ ጓደኝነት ጥሩውን ሥነ ምግባር ያበላሻል።”—1 ቆሮንቶስ 15:33 የግርጌ ማስታወሻ

    “ጓደኞችህ አንተ የምትመራባቸውን መሥፈርቶች የማይቀበሉ ከሆነ ፈጽሞ አደርገዋለሁ ብለህ አስበህ የማታውቀውን ነገር ልታደርግ ትችላለህ።”—ኤለን፣ 14

  • ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ነገሮች ገምግም

    የሚከተሉትን ጥያቄዎች ራስህን ጠይቅ፦ ‘ከጓደኞቼ ጋር ያለኝ ቅርርብ በጣም የጠበቀ ከመሆኑ የተነሳ ከእነሱ ጋር ያለኝን ጓደኝነት ላለማጣት ስል አቋሜን ለማላላት እፈተናለሁ? አንድ ጓደኛዬ መጥፎ ነገር ቢፈጽም ምን አደርጋለሁ?’

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “እኔ፣ የምወዳቸውን ሁሉ እወቅሳለሁ።”—ራእይ 3:19

    “ከቅርብ ጓደኞችህ አንዱ ችግር ላይ ቢወድቅና ለእሱ ተገቢ ያልሆነ ታማኝነት ካለህ ስለ ጉዳዩ መናገርህ እሱን አሳልፎ እንደመስጠት ሆኖ ሊሰማህ ይችላል።”—ሜላኒ፣ 22

  • ተጨማሪ ጓደኞችን ለማፍራት ጥረት አድርግ

    ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘በደንብ ከማላውቃቸው ሰዎችም ጋር ለመቀራረብ ጥረት በማድረግ ተጨማሪ ጓደኞችን ማፍራቴ የሚያስገኝልኝ ጥቅም ይኖራል?’

    የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ስለ ራሳችሁ ፍላጎት ብቻ ከማሰብ ይልቅ እያንዳንዳችሁ ለሌሎች ሰዎች ፍላጎትም ትኩረት ስጡ።”—ፊልጵስዩስ 2:4

    “በሌሎች ዘንድ ያን ያህል ተወዳጅነት የሌላቸው ልጆች ምናልባትም በቤታቸው ውስጥ ብዙ ችግሮችን ተቋቁመው የሚኖሩ ሊሆኑ ይችላሉ። አንዴ ስትቀርባቸው ግን የራሳቸው ማራኪ ባሕርይ እንዳላቸው መገንዘብህ አይቀርም።—ብራየን፣ 19

ዋናው ነጥብ፦ በጣም የምትቀርባቸው ጓደኞች ያሉህ መሆኑ ምንም ስህተት የለውም። ይሁንና ተጨማሪ ጓደኞችን ለማፍራት ጥረት ማድረግህ ይጠቅምሃል። መጽሐፍ ቅዱስ “ሌሎችን [የሚያረካ] እሱ ራሱ ይረካል” በማለት ይናገራል።—ምሳሌ 11:25

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ማርያም

“በትምህርት ቤታችን ውስጥ ካለ አንድ ቡድን ጋር እቀራረብ ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን በቡድኑ ውስጥ ካሉት ልጆች መካከል አንዳንዶቹ ሌሎች ልጆችን እንደሚያስፈራሩ አወቅኩ፤ ስለዚህ ከቡድኑ ተለይቼ ወጣሁ። እርግጥ ለተወሰነ ጊዜ ምንም ጓደኛ አልነበረኝም ማለት ይቻላል፤ ሆኖም ለማምንበት ነገር ስል እርምጃ መውሰዴ አስደስቶኛል።”—ማርያም

አሌክስ

“በትምህርት ቤት፣ በሌሎች ዘንድ ይበልጥ ተወዳጅ ለመሆን ስል ብቻ ከሆነ ቡድን ጋር ለመቀላቀል እሞክር ነበር። ሆኖም ጥሩ ካልሆኑ ልጆች ጋር ጓደኛ መሆን ለሰዎች መጥፎ አመለካከት እንድታዳብርና ያልሆንከውን ሆነህ ለመገኘት እንድትጥር ሊያደርግህ እንደሚችል ተገንዝቤያለሁ።”—አሌክስ

ቤታኒ

“የመለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳለሁ ቡድናቸውን እንድቀላቀል ከማይፈልጉ ልጆች ጋር ለመቀራረብ በጣም ጥረት አደርግ ነበር። ጥረቴ እንዳልተሳካ ስረዳ ቀድሞ የነበሩኝን ጓደኞች ማድነቅ ጀመርኩ።”—ቤታኒ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ