የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwyp ርዕስ 69
  • መጸለይ ጥቅም አለው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጸለይ ጥቅም አለው?
  • የወጣቶች ጥያቄ
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጸሎት ምንድን ነው?
  • አምላክ ጸሎቴን ይሰማል?
  • ስለ ምን ነገር መጸለይ እችላለሁ?
  • በጸሎት አማካኝነት ወደ አምላክ ቅረብ
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • ወደ አምላክ የመጸለይ ውድ መብት
    መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
  • ከአምላክ ጋር መቀራረብ የምትችለው እንዴት ነው?
    ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውቀት
  • በጸሎት አማካኝነት ከአምላክ ጋር ያለህን ዝምድና አጠናክር
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የወጣቶች ጥያቄ
ijwyp ርዕስ 69
ሐይቅ ዳርቻ የተቀመጠች ወጣት

የወጣቶች ጥያቄ

መጸለይ ጥቅም አለው?

አንድ ጥናት እንደሚያሳየው፣ በአሜሪካ 80 በመቶ የሚሆኑ ወጣቶች የሚጸልዩ ቢሆንም ከእነዚህ ወጣቶች መካከል በየዕለቱ የሚጸልዩት ግማሽ ያህሉ ብቻ ናቸው። በመሆኑም አንዳንዶች ‘ጸሎት አእምሮን ከማረጋጋት ያለፈ ጥቅም አለው?’ ብለው መጠየቃቸው ምንም አያስገርምም።

  • ጸሎት ምንድን ነው?

  • አምላክ ጸሎቴን ይሰማል?

  • ስለ ምን ነገር መጸለይ እችላለሁ?

  • እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ጸሎት ምንድን ነው?

ጸሎት የሁሉ ነገር ፈጣሪ ከሆነው አምላካችን ጋር የምንነጋገርበት መንገድ ነው። ይህ ምን ማለት እንደሆነ እስቲ አስበው! ይሖዋ በማንኛውም መንገድ ከሰው ልጆች የላቀ ነው፣ ሆኖም ‘እሱ ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።’ (የሐዋርያት ሥራ 17:27) እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “ወደ አምላክ ቅረቡ፤ እሱም ወደ እናንተ ይቀርባል” የሚል አስደናቂ ግብዣ ይዟል።—ያዕቆብ 4:8

ወደ አምላክ መቅረብ የምትችለው እንዴት ነው?

  • አንደኛው መንገድ ጸሎት ነው። ይህ አምላክን የምታነጋግርበት መንገድ ነው።

  • ሌላው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ነው። ይህ ደግሞ አምላክ አንተን ‘የሚያነጋግርበት’ መንገድ ነው።

ይህን የመሰለው የሐሳብ ግንኙነት ማለትም መጸለይህና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናትህ ከአምላክ ጋር ጠንካራ ወዳጅነት ለመመሥረት ይረዳሃል።

‘የሰው ልጆች ካገኟቸው እጅግ የላቁ መብቶች አንዱ ከልዑሉ አምላክ ከይሖዋ ጋር መነጋገር መቻል ነው።” —ጄረሚ

“ለይሖዋ በጸሎት አማካኝነት የውስጤን አውጥቼ ስናገር ወደ እርሱ ይበልጥ እንደቀረብኩ ይሰማኛል።”—ሚራንዳ

አምላክ ጸሎቴን ይሰማል?

በአምላክ የምታምን እንዲሁም ወደ እሱ የምትጸልይ ቢሆንም እንኳ ‘በእርግጥ አምላክ ጸሎቴን ይሰማል?’ የሚል ጥያቄ ሊፈጠርብህ ይችላል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ ይሖዋን “ጸሎት ሰሚ [የሆነ] አምላክ” በማለት ይጠራዋል። (መዝሙር 65:2) እንዲያውም “የሚያስጨንቃችሁንም ነገር ሁሉ በእሱ ላይ ጣሉ” በማለት ይጋብዘናል። ለምን? “ምክንያቱም እሱ ስለ [እኛ] ያስባል።”—1 ጴጥሮስ 5:7

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ ከቅርብ ጓደኞችህ ጋር ዘወትር ለመገናኘት ጊዜ ትመድባለህ? ከአምላክ ጋር ለመነጋገርም እንዲሁ ማድረግ ትችላለህ። አዘውትረህ ወደ አምላክ ጸልይ፤ ይህን ስታደርግ ይሖዋ የሚለውን ስሙን ተጠቀም። (መዝሙር 86:5-7፤ 88:9) ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ “ዘወትር ጸልዩ” በማለት ጋብዞናል።—1 ተሰሎንቄ 5:17

“ጸሎት፣ የውስጤን ሁሉ አውጥቼ የምነግረውን የሰማዩን አባቴን የማነጋግርበት መንገድ ነው።”—ሞኢስስ

“ከእናቴ ወይም ከቅርብ ጓደኞቼ ጋር ስነጋገር ሐሳቤን በዝርዝር እንደምነግራቸው ሁሉ ለይሖዋም ሁሉን ነገር በዝርዝር እነግረዋለሁ።”—ካረን

ስለ ምን ነገር መጸለይ እችላለሁ?

መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “ስለ ምንም ነገር አትጨነቁ፤ ከዚህ ይልቅ ስለ ሁሉም ነገር በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር ልመናችሁን ለአምላክ አቅርቡ።”—ፊልጵስዩስ 4:6

ታዲያ ችግሮችህን በተመለከተ ልትጸልይ ትችላለህ ማለት ነው? አዎ! እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ “ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤ እሱም ይደግፍሃል” ይላል።—መዝሙር 55:22

ለአምላክ የምታቀርበው ጸሎት ችግሮችህን ብቻ ከመግለጽ ያለፈ መሆን እንዳለበት ግልጽ ነው። ቻንቴል የተባለች አንዲት ወጣት እንዲህ ብላለች፦ “ወደ ይሖዋ የምጸልየው እንዲረዳኝ ስፈልግ ብቻ ቢሆን ኖሮ ጥሩ ወዳጅነት አለን ሊባል አይችልም ነበር። ምስጋና መቅደም እንዳለበት ይሰማኛል፤ እንዲሁም እሱን ለማመስገን የሚያነሳሱ ብዙ ነገሮች ሊኖሩኝ እንደሚገባ አምናለሁ።”

ሊታሰብበት የሚገባ ነጥብ፦ በሕይወትህ ውስጥ አምላክን ለማመስገን የሚያነሳሱህ ምን ነገሮች አሉ? በዛሬው ዕለት ይሖዋን እንድታመሰግነው የሚያነሳሱ ሦስት ነገሮችን ማሰብ ትችላለህ?

“የሚያምር አበባ አይቶ ማድነቅን የመሰለ ቀላል ነገር እንኳ ለይሖዋ የምስጋና ጸሎት እንድናቀርብ ያነሳሳናል።”—አኒታ

“በፍጥረት ሥራዎች ላይ ወይም ልባችሁን በሚነካ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላይ አሰላስሉ፣ ከዚያም ስለ ጉዳዩ ይሖዋን አመስግኑት።”—ብራያን

እኩዮችህ ምን ይላሉ?

ሞኢስስ

“የጸሎታችን ጥልቀት እንደ ትንሽ የውኃ ጉድጓድ ሳይሆን እንደ ውቅያኖስ መሆን ይኖርበታል። ይሖዋ ሊረዳን ይፈልጋል፤ እንዲሁም እሱን ከመጠየቃችን በፊትም እንኳን ምን እንደሚያፈልገን ያውቃል። ሆኖም ጥልቀት ያለው ጸሎት በመጸለይ በእሱ ምን ያህል እንደምንተማመን ማሳየት እንችላለን።”—ሞኢስስ

ሚራንዳ

“ጸሎት በአንደኛው ጫፍ ይሖዋ በሌላኛው ጫፍ ደግሞ እኔ ከያዝኩት ገመድ ጋር ይመሳሰላል። የውስጤን አውጥቼ ለይሖዋ በጸሎት ስነግረው ገመዱን አጥብቄ የያዝኩት ያህል ነው። ይሖዋ የሚሰጠኝ መልስ ደግሞ በመካከላችን ያለው ዝምድና ይበልጥ ጥብቅ እንዲሆን ያደርጋል።”—ሚራንዳ

ጄረሚ

“ካልተጠነቀቅን ጸሎታችን ልመና ብቻ ሆኖ ይቀራል። ሆኖም ይሖዋን ማመስገናችን፣ ለሰጠን በርካታ ነገሮች አድናቆት እንዲኖረን እና ጸሎታችን በእኛ ላይ ብቻ ያተኮረ እንዳይሆን ይረዳናል።—ጄረሚ

ሼልቢ

“ይሖዋን አዘውትረን ባመሰገንን ቁጥር ይበልጥ አድናቂዎች እንሆናለን። ይሖዋን በጸሎት ማመስገናችን ትኩረታችንን በሚያጋጥሙን ችግሮች ላይ ሳይሆን ባገኝናቸው በረከቶች ላይ እንድናደርግ ይረዳናል።”—ሼልቢ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ