የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 134
  • መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ መውደድ ምን ይላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ መውደድ ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ጎረቤትን መውደድ ሲባል ምን ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
  • የሚወድህን አምላክ ውደደው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ፍቅራችሁ ምን ያህል ሰፊ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 134
አንድ ወጣት ራሱን በመስተዋት ሲመለከት

መጽሐፍ ቅዱስ ራስን ስለ መውደድ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ራስን በተገቢው መጠን መውደድ ስህተት እንዳልሆነ እንዲያውም አስፈላጊ እንደሆነ ይጠቁማል። ራስን መውደድ ራስን መንከባከብንና ማክበርን እንዲሁም ለራስ ተገቢ አመለካከት መያዝን ያካትታል። (ማቴዎስ 10:31) መጽሐፍ ቅዱስ ራስ ወዳድነትን ከማበረታታት ይልቅ በተገቢው መጠን ራሳችንን መውደድ የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስገነዝበናል።

ከሁሉ አስበልጠን ልንወድ የሚገባው ማንን ነው?

  1. ከሁሉ አስበልጠን ልንወድ የሚገባው አምላክን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ከሁሉ የሚበልጠው ትእዛዝ “አምላክህን ይሖዋን በሙሉ ልብህ . . . ውደድ” የሚለው እንደሆነ ይናገራል።—ማርቆስ 12:28-35፤ ዘዳግም 6:5

  2. ሁለተኛው ታላቅ ትእዛዝ ደግሞ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ነው።—ማርቆስ 12:31፤ ዘሌዋውያን 19:18

  3. መጽሐፍ ቅዱስ ራሳችንን እንድንወድ በቀጥታ ባያዘንም “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ” የሚለው ትእዛዝ ራሳችንን በተወሰነ ደረጃም ቢሆን መውደድና ማክበር እንዳለብን እንዲሁም ይህን ማድረጋችን ተገቢ ብሎም ጠቃሚ እንደሆነ ይጠቁማል።

ኢየሱስ ከሁሉ አስበልጦ ይወድ የነበረው ማንን ነው?

ኢየሱስ አምላክን፣ ባልንጀራን ወይም ራስን ከመውደድ ሊቀድም የሚገባው የቱ እንደሆነ በገዛ በሕይወቱ አሳይቷል፤ ተከታዮቹም የእሱን ምሳሌ እንዲከተሉ አስተምሯል።—ዮሐንስ 13:34, 35

  1. ኢየሱስ ይሖዋ አምላክን ከሁሉ አስበልጦ ይወድ የነበረ ሲሆን ሕይወቱንም የእሱን ፈቃድ ለመፈጸም ተጠቅሞበታል። “እኔ አብን እንደምወድ ዓለም እንዲያውቅ አብ ባዘዘኝ መሠረት እየሠራሁ ነው” በማለት ተናግሯል።—ዮሐንስ 14:31

  2. ኢየሱስ ባልንጀሮቹን ይወድ ነበር፤ ሌሎች የሚያስፈልጋቸውን በማሟላት አልፎ ተርፎም ሕይወቱን ጭምር አሳልፎ በመስጠት ይህን ፍቅሩን አሳይቷል።—ማቴዎስ 20:28

  3. በተገቢው መጠን ራሱን እንደሚወድም አሳይቷል፤ እረፍት ለማድረግ፣ ምግብ ለመመገብ እንዲሁም ከተከታዮቹና ደቀ መዛሙርቱ መሆን ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር አብሮ ለመሆን ጊዜ ይመድብ ነበር።—ማርቆስ 6:31, 32፤ ሉቃስ 5:29፤ ዮሐንስ 2:1, 2፤ 12:2

ሌሎችን ከራሳችን አስበልጠን መውደዳችን ደስታችንን ወይም ለራሳችን ያለንን አክብሮት ይቀንሰዋል?

በፍጹም! ምክንያቱም የተፈጠርነው በአምላክ መልክ ነው፤ የአምላክ ዋነኛ ባሕርይ ደግሞ ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ፍቅር ነው። (ዘፍጥረት 1:27፤ 1 ዮሐንስ 4:8) በመሆኑም የተፈጠርነው ለሌሎች ፍቅር እንድናሳይ ተደርገን ነው። ተገቢ በሆነ መጠን ራሳችንን መውደዳችን ስህተት ባይሆንም ይበልጥ ደስተኛ የምንሆነው ከሁሉ አስበልጠን አምላክን ስንወድና ለሌሎች መልካም ነገሮችን ስናደርግ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚለው “ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበለጠ ደስታ ያስገኛል።”—የሐዋርያት ሥራ 20:35

በዛሬው ጊዜ ያሉ በርካታ ሰዎች ደስታ የሚገኘው የራስን ፍላጎት በማስቀደም እንደሆነ ይሰማቸዋል። እነዚህ ሰዎች ‘ባልንጀራህን ውደድ’ የሚለውን ትእዛዝ ወደ ጎን ገሸሽ በማድረግ ‘ራስህን ውደድ’ የሚለውን መርህ ለመከተል መርጠዋል። ይሁንና በዘመናችን የተደረጉ ጥናቶች እንዳረጋገጡት የተሻለ ጤናና ደስታ ያላቸው “እያንዳንዱ ሰው ምንጊዜም የራሱን ጥቅም ሳይሆን የሌላውን ሰው ጥቅም ይፈልግ” የሚለውን ጥበብ ያዘለ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክር በሥራ ላይ የሚያውሉ ሰዎች ናቸው።—1 ቆሮንቶስ 10:24

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ