የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 140
  • ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • የይሖዋ ምሥክሮች የሚድኑት እነሱ ብቻ እንደሆኑ ያምናሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ለመዳን ምን ማድረግ አለብን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • መጽሐፍ ቅዱስ ‘አንዴ የዳነ ለሁልጊዜው እንደዳነ’ ያስተምራል?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • መዳን በእርግጥ ምን ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 140
ኢየሱስ የተለያየ ዘር ባላቸው ሰዎች ተከቦ

ኢየሱስ ያድናል—እንዴት?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ኢየሱስ ሕይወቱን ቤዛዊ መሥዋዕት አድርጎ በመስጠት ታማኝ የሰው ልጆች የሚድኑበትን መንገድ ከፍቷል። (ማቴዎስ 20:28) በዚህም ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን “የዓለም አዳኝ” በማለት ይጠራዋል። (1 ዮሐንስ 4:14) በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦ “መዳን በሌላ በማንም አይገኝም፤ ምክንያቱም ልንድንበት የምንችል ከሰማይ በታች ለሰዎች የተሰጠ ሌላ ስም የለም።”—የሐዋርያት ሥራ 4:12

ኢየሱስ በእሱ ለሚያምን “ሰው ሁሉ ሲል ሞትን ቀምሷል።” (ዕብራውያን 2:9፤ ዮሐንስ 3:16) ከዚያም ‘አምላክ ከሞት አስነስቶት’ መንፈሳዊ ፍጡር ሆኖ ወደ ሰማይ ተመልሷል። (የሐዋርያት ሥራ 3:15) በመሆኑም ኢየሱስ “[ለሰው ልጆች] ለመማለድ ሁልጊዜ ሕያው ሆኖ ስለሚኖር በእሱ አማካኝነት ወደ አምላክ የሚቀርቡትን ፈጽሞ ሊያድናቸውም ይችላል።”—ዕብራውያን 7:25

የኢየሱስ አማላጅነት የሚያስፈልገን ለምንድን ነው?

ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን። (ሮም 3:23) ኃጢአት ከአምላክ ያራቀን ሲሆን ወደ ሞትም ይመራናል። (ሮም 6:23) ይሁን እንጂ ኢየሱስ በእሱ ቤዛዊ መሥዋዕት ለሚያምኑት “ጠበቃ” ሆኖ ያገለግላል። (1 ዮሐንስ 2:1፣ ግርጌ) አምላክ ጸሎታቸውን እንዲሰማቸውና ለሠሩት ኃጢአት በቤዛው አማካኝነት ይቅርታ እንዲያደርግላቸው ኢየሱስ ለሰው ልጆች ይማልድላቸዋል። (ማቴዎስ 1:21፤ ሮም 8:34) ኢየሱስ የሚያቀርበው ምልጃ ከአምላክ ፈቃድ ጋር ስለሚስማማ አምላክ ይቀበለዋል። ደግሞም አምላክ ኢየሱስን ወደ ምድር የላከው “ዓለም በእሱ አማካኝነት እንዲድን ነው።”—ዮሐንስ 3:17

ለመዳን የሚያስፈልገን በኢየሱስ ማመን ብቻ ነው?

አይደለም። ለመዳን በኢየሱስ ማመናችን አስፈላጊ ቢሆንም ከዚያ የበለጠ ነገር ማድረግ ይኖርብናል። (የሐዋርያት ሥራ 16:30, 31) መጽሐፍ ቅዱስ “አካል ያለመንፈስ የሞተ እንደሆነ ሁሉ እምነትም ያለሥራ የሞተ ነው” ይላል። (ያዕቆብ 2:26) ለመዳን የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ ያስፈልገናል፦

  • ስለ ኢየሱስ እና ስለ አባቱ ስለ ይሖዋ መማር።—ዮሐንስ 17:3

  • በይሖዋና በኢየሱስ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር።—ዮሐንስ 12:44፤ 14:1

  • ይሖዋና ኢየሱስ የሰጡንን ትእዛዛት በማክበር እምነት እንዳለን ማሳየት። (ሉቃስ 6:46፤ 1 ዮሐንስ 2:17) ኢየሱስ፣ የሚድኑት “ጌታ ሆይ” የሚሉት ሳይሆኑ ‘በሰማያት ያለውን የአባቱን ፈቃድ የሚያደርጉ ሰዎች ብቻ’ እንደሆኑ ተናግሯል።—ማቴዎስ 7:21

  • አስቸጋሪ ሁኔታዎች ቢያጋጥሙንም ምንጊዜም እምነት እንዳለን ማሳየት። ኢየሱስ ስለዚህ ጉዳይ ሲናገር “እስከ መጨረሻው የጸና ግን ይድናል” ብሏል።—ማቴዎስ 24:13

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ