የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 143
  • ማጨስ ኃጢአት ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ማጨስ ኃጢአት ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • መጽሐፍ ቅዱስ ለመዝናናት ሲባል ማሪዋና ወይም ሌላ ዓይነት ዕፅ ስለ መውሰድ የሚናገረው ነገር አለ?
  • ከሲጋራ ትርቃለህን?
    ንቁ!—1997
  • ስለ ሲጋራ ምን ማወቅ ይኖርብኛል?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
  • ትንባሆ ማጨስ ከአምላክ ጋር ያለኝን ግንኙነት ይነካብኛል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ማጨስ በአምላክ ዘንድ እንዴት ይታያል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 143
ሲጋራ ማጨስ

ማጨስ ኃጢአት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ማጨስምa ሆነ ትንባሆን በሌሎች መንገዶች ስለ መጠቀም አይናገርም። ሆኖም ጤናን የሚጎዱና ንጹሕ ያልሆኑ ልማዶች በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት እንደሌላቸው የሚገልጹ መመሪያዎችን ይዟል፤ በመሆኑም ማጨስ በአምላክ ዘንድ ኃጢአት ነው።

  • ለሕይወት አክብሮት ማሳየት፦ ‘ሕይወትንና እስትንፋስን ለሰው ሁሉ የሰጠው አምላክ ነው።’ (የሐዋርያት ሥራ 17:24, 25) ሕይወት ከአምላክ የተገኘ ስጦታ ስለሆነ ማጨስን ጨምሮ ዕድሜያችንን ሊያሳጥር የሚችል ማንኛውንም ነገር ከማድረግ እንቆጠባለን። ማጨስ በዓለም ዙሪያ ያሉ በርካታ ሰዎች ያለዕድሜያቸው እንዲቀጩ ከሚያደርጉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ነው።

  • ለባልንጀራችን ያለን ፍቅር፦ “ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ።” (ማቴዎስ 22:39) ሌሎች ባሉበት ቦታ ማጨስ ለእነሱ ፍቅር እንዳለን አያሳይም። እንዲያውም ለሲጋራ ጭስ የተጋለጡ ሰዎች፣ የሚያጨሱ ሰዎችን በሚያጠቁ በሽታዎች የመያዝ አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው።

  • ቅዱስ ሆኖ መኖር፦ “ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት አድርጋችሁ [አቅርቡ]።” (ሮም 12:1) “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ፤ እንዲሁም አምላክን በመፍራት ቅድስናችንን ፍጹም እናድርግ።” (2 ቆሮንቶስ 7:1) ማጨስ ሰዎች ቅዱስ ወይም ንጹሕ ሆነው እንዳይኖሩ ያደርጋል፤ ምክንያቱም የሚያጨሱ ሰዎች አካላቸውን የሚጎዱ መርዛማ ነገሮችን ሆን ብለው ወደ ሰውነታቸው ያስገባሉ።

መጽሐፍ ቅዱስ ለመዝናናት ሲባል ማሪዋና ወይም ሌላ ዓይነት ዕፅ ስለ መውሰድ የሚናገረው ነገር አለ?

መጽሐፍ ቅዱስ ማሪዋና (ዊድ ወይም ፖት ተብሎም ይጠራል) ወይም ሌላ ዓይነት ዕፅ ጠቅሶ አይናገርም። ይሁን እንጂ ሱስ የሚያስይዙ ንጥረ ነገሮችን ለመዝናኛ ብሎ መውሰድን የሚከለክሉ መመሪያዎች ይዟል። ቀደም ሲል ከተጠቀሱት መመሪያዎች በተጨማሪ የሚከተሉትም ከዚህ ጋር በተያያዘ ይሠራሉ፦

  • የማሰብ ችሎታችንን የመቆጣጠር አስፈላጊነት፦ “አምላክህን ይሖዋን . . . በሙሉ አእምሮህ ውደድ።” (ማቴዎስ 22:37, 38) “የማስተዋል ስሜታችሁን በሚገባ ጠብቁ።” (1 ጴጥሮስ 1:13) አንድ ሰው ዕፅ የሚወስድ ከሆነ የማሰብ ችሎታውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር አይችልም፤ እንዲያውም ብዙ ሰዎች የእነዚህ ዕፆች ሱሰኛ ሆነዋል። አእምሯቸው የሚያተኩረው ጥሩ በሆኑ ነገሮች ላይ ሳይሆን ዕፅ ማግኘት በሚችሉበት መንገድ ላይ ነው።—ፊልጵስዩስ 4:8

  • ለመንግሥት ባለሥልጣናት መታዘዝ፦ ‘ለመንግሥታትና ለባለሥልጣናት ታዘዙ።’ (ቲቶ 3:1) በብዙ አገራት ውስጥ አንዳንድ ዕፆችን መውሰድ በሕግ የተከለከለ ነው። አምላክን ማስደሰት የምንፈልግ ከሆነ ደግሞ የመንግሥት ባለሥልጣናትን እንታዘዛለን።—ሮም 13:1

ትንባሆ በጤና ላይ የሚያደርሰው ጉዳት

የዓለም የጤና ድርጅት በየዓመቱ ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ከትንባሆ ጋር በተያያዙ በሽታዎች ለሞት እንደሚዳረጉ ገምቷል፤ ይህ አኃዝ እነሱ ራሳቸው ባያጨሱም እንኳ ለትንባሆ ጭስ በመጋለጣቸው ብቻ ጉዳት የሚደርስባቸውን ከ600,000 የሚበልጡ ሰዎችንም ይጨምራል። ትንባሆ፣ በሚያጨሱ ሰዎችም ላይም ሆነ ለትንባሆ ጭስ በሚጋለጡ ሰዎች ላይ ምን ጉዳት እንደሚያደርስ እስቲ እንመልከት።

ካንሰር፦ የትንባሆ ጭስ በውስጡ ከ50 የሚበልጡ ካንሰር ሊያስከትሉ የሚችሉ ኬሚካሎችን ይዟል። ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደገለጸው የትንባሆ ጭስ “የሳንባ ካንሰር እንዲከሰት 90 በመቶ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይታመናል።” በተጨማሪም የትንባሆ ጭስ በአፍ፣ በአየርና በምግብ መውረጃ ቧንቧዎች፣ በጉሮሮ፣ በላንቃ፣ በጉበት፣ በቆሽት፣ በፊኛ ላይና በተለያዩ የአካል ክፍሎች ላይ ጉዳት ያደርሳል።

የመተንፈሻ አካል በሽታዎች፦ የትንባሆ ጭስ ከመተንፈሻ አካላት ጋር ተያይዘው ከሚመጡ እንደ ሳንባ ምች እና ኢንፍሉዌንዛ ባሉ የመተንፈሻ አካል በሽታዎች የመያዝ አጋጣሚን ይጨምራል። ለትንባሆ ጭስ ዘወትር የሚጋለጡ ልጆች በአስም እና ቶሎ በማይለቅ ሳል የመያዝ አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው፤ ሳንባቸው እድገት የሚያደርግበትም ሆነ የሚሠራበት መንገድም ቢሆን አዝጋሚ ይሆናል።

የልብ በሽታ፦ የሚያጨሱ ሰዎች በአንጎላቸው ውስጥ ደም የመፍሰስ ወይም በልብ በሽታ የመጠቃት አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው። በትንባሆ ጭስ ውስጥ የሚገኘው ካርቦን ሞኖክሳይድ ከሳንባ ወደ ደም ሥር በቀላሉ በመግባት ኦክስጅኑን ሊያስወግደው ይችላል። በደማችን ውስጥ ያለው ኦክስጅን አነስተኛ ከሆነ ደግሞ ወደተለያዩ የሰውነታችን ክፍሎች ኦክስጅን ለማድረስ ልባችን ከፍተኛ ሥራ ለመሥራት ይገደዳል።።

በእርግዝና ወቅት የሚያስከትለው ጉዳት፦ በእርግዝና ወቅት የሚያጨሱ ሴቶች ያለጊዜያቸው የመውለድ አጋጣሚያቸው ሰፊ ነው፤ ከዚህም ሌላ የሚወለዱት ልጆች የተሰነጠቀ ከንፈር ያላቸው፣ ክብደታቸው በጣም ዝቅተኛ የሆነ አሊያም ሌሎች የጤና እክሎች ያሉባቸው ሊሆኑ ይችላሉ። በተጨማሪም ሕፃናቱ ከመተንፈሻ አካል ጋር ለተያያዙ በሽታዎች ሊጋለጡ ብሎም በድንገት በጨቅላነታቸው ሊቀጩ ይችላሉ።

a ማጨስ ሲባል ሲጋራና ፒፓ ማጨስን፣ የትንባሆ ቅጠል ጠቅልሎ ማጨስን ወይም እንደ ሺሻ ባሉ ዕቃዎች ተጠቅሞ ማጨስን ይጨምራል። በሌላ በኩል ደግሞ እዚህ ላይ የተገለጸው ሐሳብ ትንባሆ ከማኘክ ወይም በአፍንጫ ከመሳብ እንዲሁም ኒኮቲን ያለው የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ እና ሌሎች ተመሳሳይ ነገሮችን ከመጠቀም ጋር በተያያዘም በእኩል ደረጃ ይሠራል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ