የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbv ርዕስ 3
  • ሮም 10:13—“የጌታን ስም የሚጠራ”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሮም 10:13—“የጌታን ስም የሚጠራ”
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የሮም 10:13 ትርጉም
  • የሮም 10:13 አውድ
  • ይሖዋ
    ከቅዱሳን ጽሑፎች እየጠቀሱ ማመራመር
  • የአምላክ ስምና “አዲስ ኪዳን”
    ለዘላለም ጸንቶ የሚኖረው መለኮታዊው ስም
  • የአምላክ ስም
    ንቁ!—2017
  • ሀ4 መለኮታዊው ስም በዕብራይስጥ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
ijwbv ርዕስ 3

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው

ሮም 10:13—“የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል”

“የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል።”—ሮም 10:13 አዲስ ዓለም ትርጉም

“የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል”—ሮም 10:13 የ1954 ትርጉም

የሮም 10:13 ትርጉም

አምላክ አያዳላም፤ ደግሞም ብሔር፣ ጎሳ ወይም የኑሮ ደረጃ ሳይለይ ለሁሉም ሰዎች መዳን የሚችሉበትና የዘላለም ሕይወት የሚያገኙበት አጋጣሚ ከፍቷል። ሆኖም ይህን በረከት ለማግኘት ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ የግል መጠሪያ የሆነውን ይሖዋ የሚለውን ስም መጥራት ያስፈልጋል።a—መዝሙር 83:18

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ‘የይሖዋን ስም መጥራት’ የሚለው አገላለጽ የአምላክን ስም ከማወቅና በአምልኮ ወቅት ስሙን ከመጥራት ያለፈ ነገርን ያመለክታል። (መዝሙር 116:12-14) በአምላክ መታመንንና የእሱን እርዳታ መፈለግን ይጨምራል።—መዝሙር 20:7፤ 99:6

ኢየሱስ ክርስቶስ ለአምላክ ስም ትልቅ ቦታ ይሰጥ ነበር። ባስተማረው የጸሎት ናሙና ላይ የጠቀሳቸው የመጀመሪያዎቹ ቃላት “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ” የሚሉ ናቸው። (ማቴዎስ 6:9) በተጨማሪም ኢየሱስ የዘላለም ሕይወት ማግኘት ከፈለግን ስሙ የሚወክለውን አካል ማወቅ፣ መታዘዝና መውደድ እንዳለብን አስተምሯል።—ዮሐንስ 17:3, 6, 26

የ1954 ትርጉም ሮም 10:13 ላይ “ጌታ” ብሎ የጠቀሰው አካል ይሖዋን እንደሚያመለክት እርግጠኞች መሆን የምንችለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም ይህ ጥቅስ የተወሰደው ከኢዩኤል 2:32 ላይ ሲሆን እዚያ ላይ የመጀመሪያው የዕብራይስጥ ጽሑፍ “ጌታ” የሚለውን የማዕረግ ስም ሳይሆን የአምላክን ስም በቀጥታ ይጠቅሳል።b

የሮም 10:13 አውድ

መጽሐፍ ቅዱስ በሮም ምዕራፍ 10 ላይ አንድ ሰው በአምላክ ፊት ተቀባይነት ማግኘቱ የተመካው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመኑ ላይ እንደሆነ ይጠቁማል። (ሮም 10:9) ብሉይ ኪዳን ተብለው ከሚጠሩት መጻሕፍት የተወሰዱ በርካታ ጥቅሶች ይህን ሐሳብ ይደግፋሉ። አንድ ሰው እምነት እንዳለው የሚያሳየው የሚያምንበትን ነገር አማኝ ላልሆኑ ሰዎች ‘በይፋ በመናገር’ ነው፤ በይፋ ከሚናገራቸው ነገሮች መካከል ስለ መዳን የሚገልጸው ምሥራች ይገኝበታል። ይህም ሌሎች የዘላለም ሕይወት ለማግኘት የሚያስችላቸውን እምነት የሚያዳብሩበት አጋጣሚ እንዲያገኙ ያደርጋል።—ሮም 10:10, 14, 15, 17

ሮም ምዕራፍ 10⁠ን አንብብ፤ እንዲሁም ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት የግርጌ ማስታወሻዎቹንና ማጣቀሻዎቹን ተመልከት።

a በእጅ በተገለበጡ ጥንታዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ላይ የአምላክ ስም ወደ 7,000 ጊዜ ገደማ ተጠቅሶ ይገኛል። በዕብራይስጥ የአምላክ ስም የሚጻፈው ቴትራግራማተን ተብለው በሚጠሩ አራት ፊደላት ነው። በአማርኛ የተለመደው የዚህ ስም አጠራር “ይሖዋ” ነው፤ ሆኖም አንዳንድ ምሁራን “ያህዌህ” የሚለውን አጠራር ይመርጣሉ።

b ክርስቲያን የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎች የአምላክ ስም ከሚገኝባቸው “የብሉይ ኪዳን” ክፍሎች ላይ ሲጠቅሱ ስሙን ሳይጠቀሙ አልቀሩም። ዚ አንከር ባይብል ዲክሽነሪ እንዲህ ብሏል፦ “የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት መጀመሪያ ላይ በተጻፉበት ጊዜ፣ በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ ባሉ ከብሉይ ኪዳን የተወሰዱ የተወሰኑ ወይም ሁሉም ጥቅሶች ላይ ያህዌህ የሚለውን መለኮታዊ ስም የሚወክለው ቴትራግራማተን ይገኝ እንደነበር አንዳንድ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ።” (ጥራዝ 6፣ ገጽ 392) ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት አዲስ ዓለም ትርጉም በተባለው መጽሐፍ ቅዱስ ተጨማሪ መረጃ ሀ5 ላይ የሚገኘውን “መለኮታዊው ስም በክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ” የሚለውን ርዕስ ተመልከት። ሮም 10:13 ላይ የአምላክን ስም የሚጠቀሙ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ዝርዝር አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ የጥናት እትም (እንግሊዝኛ) ላይ ማግኘት ትችላለህ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ