ተጨማሪ ሐሳብ ^ [1] (አንቀጽ 4) የጴንጤቆስጤ በዓል የሚከበርበት ጊዜ የሚውለው ሕጉ በሲና ለሕዝቡ በተሰጠበት ጊዜ ላይ ሳይሆን አይቀርም። (ዘፀ. 19:1) ይህ ከሆነ ደግሞ በሙሴ በኩል ለእስራኤላውያን የሕጉ ቃል ኪዳን የተሰጠው በዚያ ዕለት እንደሆነ ሁሉ ኢየሱስ ክርስቶስም ከአዲሱ ብሔር ወይም ከመንፈሳዊ እስራኤል ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የገባው በተመሳሳይ ዕለት ነው።