የግርጌ ማስታወሻ
a የሴቴው ክፍል የሚዳብረው ከሌላ ተክል በሚመጣ የአበባ ዱቄት (cross-pollination) አሊያም በዚያው ተክል ላይ ያለው ወንዴ ክፍል በሚያመርተው የአበባ ዱቄት (self-pollination) አማካኝነት ሊሆን ይችላል። ይሁን እንጂ ተክሉ ጤናማ የሆኑና አደጋ የመቋቋም ኃይል ያላቸውን የተለያዩ ዓይነት ፍሬዎችን ማፍራት የሚችለው ሴቴው ከሌላ ተክል በሚመጣ የአበባ ዱቄት ሲዳብር ነው።