የግርጌ ማስታወሻ
a ባይሰን የሚባለው የአውሮፓ ጎሽ ሁለት ዝርያዎች አሉት። እነሱም የቆላው የአውሮፓ ጎሽ ዝርያና የኮውኬዢያ ወይም ተራራማ ቦታዎች ላይ የሚኖረው የአውሮፓ ጎሽ ዝርያ ናቸው። የመጨረሻው የኮውኬዢያ ጎሽ የሞተው በ1927 ነበር። ይሁን እንጂ ቀደም ሲል የዚህ ጎሽ ዝርያ ከቆላ ጎሽ ጋር እንዲዳቀል በማድረግ የተዳቀለ ዝርያ ማግኘት ተችሎ ነበር። ዛሬም ጥቂት ቁጥር ያላቸው የተዳቀሉ የኮውኬዢያ ጎሾች አሉ።