የግርጌ ማስታወሻ a በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ነፍስ” የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰውየውን ራሱን እንጂ ከሥጋው ተለይታ የምትሄድን ነገር አይደለም። ዘፍጥረት 2:7 እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ ሰውን አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስ እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ሆነ።” አዳም ከሥጋው የተለየ ነፍስ አልተሰጠውም። ከዚህ ይልቅ አዳም ራሱ ሕያው ነፍስ ነበር።