የግርጌ ማስታወሻ
a የእናትየዋ ወይም የልጁ ጤና አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል የሚለው ስጋት ፅንስ ለማስወረድ ተቀባይነት ያለው ምክንያት ሊሆን አይችልም። በወሊድ ወቅት ማትረፍ የሚቻለው የእናትየዋን ወይም የልጁን ሕይወት ብቻ ከሆነ ወላጆቹ የትኛውን እንደሚመርጡ መወሰን ይኖርባቸዋል። ሆኖም በአብዛኞቹ ያደጉ አገሮች ውስጥ በሕክምናው መስክ ከፍተኛ እድገት ስለተደረገ እንዲህ ያለ ሁኔታ የሚያጋጥመው ከስንት አንዴ ነው።