የግርጌ ማስታወሻ
c በኢማኑኤል ቶቭ የተጻፈው ቴክስቹዋል ክሪቲስዝም ኦቭ ዘ ሂብሩ ባይብል እንዲህ ብሏል:- “1QISaa [የሙት ባሕር የኢሳይያስ ጥቅልል] በካርቦን 14 ሲለካ ከ202 እስከ 107 ከዘአበ የተጻፈ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። (በፓሊዮግራፊ ሲለካ ጥቅልሉ የተጻፈው ከ125-100 ከዘአበ ባለው ጊዜ ነው።) . . . በቅርብ ዓመታት በጣም የተሻሻለውና የፊደላትን ቅርጽና አቀማመጥ ዕድሜያቸው በትክክል ከታወቁ በገንዘብና በድንጋይ ጽላቶች ላይ ከተቀረጹ ፊደላት ጋር በማስተያየት የሚደረገው የፓሊዮግራፊ የዘመናት አለካክ ዘዴ በአንጻራዊ ሁኔታ አስተማማኝ ሆኖ ተገኝቷል።”6