የግርጌ ማስታወሻ
b ሰናክሬም ድል ከተደረገ በኋላ የአካባቢው ብሔራት ወርቅ፣ ብርና ሌሎችንም ውድ ነገሮች በስጦታ መልክ ለሕዝቅያስ አምጥተውለታል። በ2 ዜና መዋዕል 32:22, 23, 27 ላይ “ለሕዝቅያስም እጅግ ብዙ ሀብትና ክብር” እንደሆነለትና “በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ” እንዳለ እናነባለን። ይህ ስጦታ ምናልባት ለአሦራውያን ግብር በሰጠበት ጊዜ አራቁቶት የነበረውን ግምጃ ቤቱን ለማሟላት ሳያስችለው አልቀረም።