የግርጌ ማስታወሻ
a ኤርምያስ 52:15 ኢየሩሳሌም በባቢሎናውያን እጅ ከወደቀች በኋላ የነበረውን ሁኔታ አስመልክቶ ሲገልጽ ‘ስለ ሕዝቡ ድሆችና በከተማ ውስጥ ስለቀረው የሕዝቡ ቅሬታ ’ ተናግሯል። ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል (እንግሊዝኛ) የተባለው መጽሐፍ ጥራዝ 1 ገጽ 415 ላይ ይህን በተመለከተ የሚከተለውን አስተያየት ይሰጣል:- “ ‘በከተማ ውስጥ የቀረው’ የሚለው አነጋገር ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በረሃብ፣ በበሽታ ወይም በእሳት አሊያም በጦርነቱ እንዳለቀ ሊጠቁም ይችላል።”