የግርጌ ማስታወሻ
c የሉቃስ ወንጌል ፈተናዎቹን የሚያስቀምጥበት ቅደም ተከተል ከማቴዎስ ወንጌል የተለየ ነው። ይሁን እንጂ የማቴዎስ ዘገባ በጊዜ ቅደም ተከተል የተቀመጠ ይመስላል። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? እስቲ ሦስት ምክንያቶችን እንመልከት። (1) ማቴዎስ ሁለተኛውን ፈተና የጀመረው “ከዚያም” በማለት ነው። ይህም ቀጥሎ የተከናወነ ድርጊት እንደሆነ ይጠቁማል። (2) ሰይጣን ከአሥርቱ ትእዛዛት መካከል የመጀመሪያውን ትእዛዝ የሚያስጥሰውን ግልጽ ፈተና ያቀረበው “የአምላክ ልጅ ከሆንክ” በሚሉት ቃላት የሚጀምሩትን ሁለት ስውር ፈተናዎች ካቀረበ በኋላ ነው ብሎ ማሰብ ምክንያታዊ ይመስላል። (ዘፀ. 20:2, 3) (3) ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ!” በማለት የተናገረው ሦስተኛውና የመጨረሻው ፈተና በቀረበለት ጊዜ ነው የሚለው ሐሳብ ይበልጥ አሳማኝ ነው።—ማቴ. 4:5, 10, 11