የግርጌ ማስታወሻ
a ሆስፒታል ውስጥ የሚሠሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች እንዲህ ዓይነቱን ሥልጣን ማጤን አስፈልጓቸዋል። አንድ ታካሚ ሊወስዳቸው የሚገቡ መድኃኒቶችን ወይም ሊከተል የሚገባውን የሕክምና ሂደት በተመለከተ አንድ ሐኪም የመወሰን መብት ሊኖረው ይችል ይሆናል። ምንም እንኳ ታካሚው ባይቃወምም የመወሰን ሥልጣን ያለው ዶክተር የሆነ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ የሚለውን እያወቀ ታካሚው ደም እንዲሰጠው ወይም ውርጃ እንዲፈጸም እንዴት ትእዛዝ ሊሰጥ ይችላል? በአንጻሩ ደግሞ ሆስፒታሉ ውስጥ ተቀጥራ የምትሠራ አንዲት ነርስ ይህ ዓይነቱ ሥልጣን ላይኖራት ይችላል። የተለመደውን ተግባሯን ስታከናውን አንድ ዶክተር ለሆነ ዓላማ የደም ምርመራ እንድታደርግ ወይም ጽንስ ለማስወረድ የመጣችን ታካሚ እንድትረዳ ያዝዛት ይሆናል። በ2 ነገሥት 5:17-19 ላይ ሰፍሮ ከሚገኘው ምሳሌ ጋር በሚስማማ መንገድ ደም እንዲሰጥ የማዘዝ ሥልጣን እስከሌላት ወይም ጽንስ ማስወረዱ እንዲፈጸም እስካላደረገች ድረስ ለታካሚው ሰብዓዊ አገልግሎቶችን መስጠት እንደምትችል ይሰማት ይሆናል። እርግጥ፣ አሁንም ቢሆን ‘በመልካም ሕሊና ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት መኖር’ እንድትችል ሕሊናዋን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባት።—ሥራ 23:1