የግርጌ ማስታወሻ
b ከዚህ ጋር ተዛማጅነት ያለው የሚመስል አንድ ሌላ ሕግ ደግሞ ብልቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት ወንድ ፈጽሞ ወደ አምላክ ጉባኤ መግባት እንደሌለበት ይናገራል። (ዘዳግም 23:1) ሆኖም ቅዱሳን ጽሑፎችን ጠለቅ ብሎ ማስተዋል ይህ ሁኔታ “እንደ ግብረ ሰዶም ለመሳሰሉ ርኩስ ዓላማዎች ሆን ተብሎ ከማኮላሸት ጋር ግንኙነት ያለው መሆኑ” ግልጽ እንደሆነ ጠቅሷል። ከዚህ የተነሳ ይህ ሕግ ማኮላሸትን ወይም ከማኮላሸት የማይተናነስ ድርጊትን የወሊድ መቆጣጠሪያ አድርጎ አላካተተም። በተጨማሪም ማስተዋል እንዲህ ይላል:- “ይሖዋ ጃንደረባዎች የእርሱ አገልጋዮች እንደሆኑ በመቁጠር በእርሱ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣና ታዛዥ ከሆኑ ደግሞ ከወንዶችና ከሴቶች ልጆች የሚበልጥ ስም እንደሚያገኙ በሚያጽናና መንገድ በትንቢት ተናግሯል። በኢየሱስ ክርስቶስ አማካኝነት ሕጉ ሲወገድ እምነት ያላቸው ሰዎች በሙሉ ቀድሞ የነበራቸው አቋም ወይም ሁኔታ ምንም ይሁን ምን የአምላክ መንፈሳዊ ልጆች መሆን ችለዋል። ሥጋዊ ልዩነቶች ተወግደው ነበር።—ኢሳ 56:4, 5፤ ዮሐ 1:12”