የግርጌ ማስታወሻ a የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን ጽሑፎች መዝሙር 91ን ከመሲሐዊ ትንቢት አንጻር ጠቅሰው አልተናገሩም። እርግጥ ነው፣ ይሖዋ ለኢየሱስ ክርስቶስ መሸሸጊያና ጠንካራ ምሽግ እንደሆነለት ሁሉ ለኢየሱስ ቅቡዓን ተከታዮችና ራሳቸውን ለአምላክ ለወሰኑት ጓደኞቻቸው በዚህ ‘የፍጻሜ ዘመን’ በቡድን ደረጃ መሸሸጊያና ጠንካራ ምሽግ ይሆንላቸዋል።—ዳንኤል 12:4