የግርጌ ማስታወሻ
b ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም አንዳንዶች ቤተ መቅደሱ የዳጋን ሳይሆን የኤል ነው ይላሉ። በኢየሩሳሌም የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ትምህርት ቤት ፕሮፌሰር የሆኑት ፈረንሳዊው ምሁር ሮናልድ ደ ቮ በመሳፍንት 16:23 እና በ1 ሳሙኤል 5:1-5 ላይ ዳጎን ተብሎ የተጠራው ዳጋን የኤል መጠሪያ ስም ነው የሚል ሐሳብ አላቸው። ዚ ኢንሳይክሎፒዲያ ኦቭ ሪሊጅን “ዳጋን እና ኤል አንድ ዓይነት ዝምድና” ሳይኖራቸው እንደማይቀር ይናገራል። በራስ ሻምራ ጽሑፎች ላይ በኣል የዳጋን ልጅ ተብሎ ተጠርቷል። ቢሆንም “ልጅ” የሚለው ቃል ምን እንደሚያመለክት ግልጽ አይደለም።