የግርጌ ማስታወሻ
a ኢየሱስ እንደሰጠው የናሙና ጸሎት ሁሉ የሐዘንተኛ ካዲሽ የተባለው ጸሎትም የአምላክ ስም እንዲቀደስ ይጠይቃል። ይህ ጸሎት በክርስቶስ ዘመን እንዲያውም ከዚያ ቀደም ብሎ የነበረ ስለመሆኑ ውዝግብ ቢኖርም ኢየሱስ ከሰጠው የናሙና ጸሎት ጋር መመሳሰሉ ሊያስገርመን አይገባም። ኢየሱስ የሰጠው ጸሎት አዲስና የተለየ ሐሳብ የያዘ አልነበረም። በጸሎቱ ውስጥ የተካተተው እያንዳንዱ ልመና ሁሉም አይሁዳውያን በወቅቱ በነበሯቸው ቅዱሳን መጻሕፍት ላይ ሙሉ በሙሉ የተመሠረተ ነበር። ኢየሱስ፣ አይሁዳውያኑ እሱ ከመምጣቱ በፊት ሊጸልዩለት ይገባ የነበረውን ነገር እንዲለምኑ ማበረታታቱ ነበር።