የግርጌ ማስታወሻ
a የኢየሱስ አነጋገር፣ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች “መገኘት” የሚለውን ቃል የተረጎሙበት መንገድ የሚያስተላልፈውን የተሳሳተ ሐሳብ ለማስተካከል ያስችላል። እንደ አማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ ያሉ አንዳንድ ትርጉሞች ይህን ቃል “መምጣት፣” “ምጽዓት” ወይም “መመለስ” ብለው ያስቀመጡት ሲሆን እነዚህ ቃላት ደግሞ አጠር ያለ ጊዜ ያመለክታሉ። ሆኖም ኢየሱስ፣ መገኘቱን ያመሳሰለው ‘ከኖኅ ዘመን’ ጋር እንጂ በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው የጥፋት ውኃ ጋር እንዳልሆነ ልብ በል፤ የጥፋት ውኃው አንድ ጊዜ የተፈጸመ ክስተት ሲሆን የኖኅ ዘመን ግን ታላቅ ክንውን የተፈጸመበት ወቅት ነበር። ልክ እንደ ኖኅ ዘመን ሁሉ በክርስቶስ መገኘት ወቅትም ሰዎች በዕለት ተዕለት የሕይወት ጉዳዮቻቸው በጣም ስለሚጠላለፉ የሚሰጣቸውን ማስጠንቀቂያ ልብ አይሉም።