የግርጌ ማስታወሻ
a ዮናስ የተወለደው በገሊላ በምትገኝ ከተማ ውስጥ መሆኑ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው፤ ምክንያቱም ፈሪሳውያን በአንድ ወቅት ስለ ኢየሱስ ሲናገሩ በእብሪተኝነት መንፈስ “ከገሊላ አንድም ነቢይ እንደማይነሳ መርምረህ ተረዳ” ብለው ነበር። (ዮሐንስ 7:52) በርካታ ተርጓሚዎችና ተመራማሪዎች፣ ፈሪሳውያን ዝቅ ተደርጋ ከምትታየው ከገሊላ ነቢይ ተነስቶ አያውቅም፣ ወደፊትም አይነሳም የሚል ጭፍን አመለካከት እንደነበራቸው ገልጸዋል። እነዚህ ሰዎች እንዲህ ዓይነት አመለካከት ከነበራቸው ታሪክንም ሆነ ትንቢትን ወደ ጎን ገሸሽ አድርገው ነበር ማለት ነው።—ኢሳይያስ 9:1, 2