የግርጌ ማስታወሻ
a ለመሥዋዕት የሚቀርብ አንድ እንስሳ፣ ኃጢአት የማስተሰረይ ኃይሉ ያለው አምላክ እንደ ቅዱስ አድርጎ በሚመለከተው በደሙ ላይ ነው። (ዘሌዋውያን 17:11) ታዲያ ይህ ሲባል ድሆች የሚያቀርቡት የዱቄት መሥዋዕት ዋጋ የለውም ማለት ነው? በፍጹም። ይሖዋ፣ አንድ እስራኤላዊ እንዲህ ያለውን መሥዋዕት እንዲያቀርብ ያነሳሳውን የትሕትናና የፈቃደኝነት መንፈስ እንደሚያደንቅ ብሎም ትልቅ ቦታ እንደሚሰጠው ጥርጥር የለውም። ከዚህም ሌላ ድሆችን ጨምሮ የመላው ብሔር ኃጢአት በዓመታዊው የስርየት ቀን ለአምላክ በሚቀርቡት የእንስሳት ደም ይሸፈን ነበር።—ዘሌዋውያን 16:29, 30