የግርጌ ማስታወሻ
c ካህናቱ የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች ይንቁ እንደነበር የሚያሳዩ ሁለት ምሳሌዎችን ከዘገባው መመልከት ይቻላል። በመጀመሪያ ደረጃ፣ ሕጉ ከመሥዋዕቱ ውስጥ የካህናቱ ድርሻ የትኛው እንደሆነ ለይቶ ይገልጽ ነበር። (ዘዳግም 18:3) ክፉዎቹ ካህናት በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚከተሉት አሠራር ግን ከዚህ በጣም የተለየ ነበር። ካህናቱ፣ ሥጋው እየተቀቀለ ሳለ አገልጋዮቻቸውን በመላክ ከድስቱ ውስጥ ማንኛውንም ምርጥ ሥጋ በሜንጦ አውጥተው እንዲያመጡላቸው ያደርጉ ነበር! ሌላው ደግሞ ሕዝቡ መሥዋዕታቸውን በመሠዊያው ላይ እንዲቃጠልላቸው ሲያመጡ ክፉዎቹ ካህናት የመሥዋዕቱ ስብ ገና ለይሖዋ ከመቅረቡ በፊት አገልጋያቸው መሥዋዕት የሚያቀርበውን ሰው አስገድዶ ጥሬ ሥጋ እንዲያመጣላቸው ያደርጉ ነበር።—ዘሌዋውያን 3:3-5፤ 1 ሳሙኤል 2:13-17