የግርጌ ማስታወሻ
d “ሁለተኛው የባቢሎን አገዛዝ” ተብሎ በሚታመነው ዘመን በሙሉ በእያንዳንዱ ዓመት የተዘጋጁ የንግድ ጽላቶች ተገኝተዋል። እነዚህ ነገሥታት የገዙባቸው ዓመታት ከተደመሩ በኋላ “የሁለተኛው የባቢሎን አገዛዝ” የመጨረሻ ንጉሥ ከሆነው ከናቦኒደስ አንስቶ ወደኋላ ሲሰላ ኢየሩሳሌም የጠፋችው በ587 ዓ.ዓ. ነው የሚለው መደምደሚያ ላይ ይደረሳል። ይሁን እንጂ ይህ የዘመናት ስሌት ትክክል የሚሆነው እያንዳንዱ ንጉሥ ቀጣዩን ተክቶ ሥልጣን ላይ የወጣው በዚያው ዓመት ከሆነ ብቻ ነው።