የግርጌ ማስታወሻ
b ዘሞራ ለሮም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ባቀረበው አቤቱታ ላይ የአምላክን የማዕረግ ስም ሳይሆን መለኮታዊውን ስም መጠቀሙ ልብ ሊባል ይገባዋል። ወደ ስፓንኛ በተተረጎመው የዘሞራ አቤቱታ ላይ መለኮታዊው ስም “ያህዌህ” ተብሎ ተገልጿል። በላቲን በተጻፈው በመጀመሪያው አቤቱታ ላይ ይህ ስም እንዴት እንደተቀመጠ በእርግጠኝነት አይታወቅም። የዘሞራን ትርጉምና በመለኮታዊው ስም መጠቀሙን በተመለከተ በገጽ 19 ላይ የሚገኘውን “መለኮታዊውን ስም መተርጎም” የሚለውን ሣጥን ተመልከት።