የግርጌ ማስታወሻ
a “አፖክሪፋ” የሚለው ቃል የመጣው “መሰወር” የሚል ትርጉም ካለው የግሪክኛ ቃል ነው። ቃሉ በመጀመሪያ ያመለክት የነበረው ተመሳሳይ አስተሳሰብ ያላቸውን ሰዎች ላቀፈ አንድ ቡድን አባላት ብቻ የተዘጋጀ ጽሑፍን ሲሆን የዚህ ቡድን አባል ላልሆኑ ሰዎች ጽሑፉ የተሰወረ ነበር። ከጊዜ በኋላ ግን ይህ ቃል፣ በአምላክ መንፈስ መሪነት እንደተጻፉ ተቀባይነት ባገኙት የቅዱሳን መጻሕፍት ዝርዝር ውስጥ ያልተካተቱ ጽሑፎችን ያመለክት ጀመር።