የግርጌ ማስታወሻ
a በማደግ ላይ ያለው ሽል ጤነኛ ባይመስል ወይም በርካታ ሽሎች በማህፀን ውስጥ ማደግ ቢጀምሩስ? ሆን ብሎ ፅንስ እንዲቋረጥ ማድረግ ውርጃ መፈጸም ይሆናል። በአይ ቪ ኤፍ ዘዴ የሚጠቀሙ ሴቶች ብዙውን ጊዜ ሁለት፣ ሦስት ወይም ከዚያ የሚበልጡ መንትዮች ሊወልዱ ይችላሉ፤ ይህ ደግሞ እናትየው ቀኑ ያልደረሰ ሕፃን የመውለዷ ወይም በሰውነቷ ውስጥ ብዙ ደም የመፍሰሱ አጋጣሚ ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል። በማህፀኗ ውስጥ ብዙ ሽሎች የያዘች እናት አንድ ወይም ከዚያ በላይ ሽሎች “ተመርጠው እንዲወገዱ” ይኸውም እንዲገደሉ እንድትፈቅድ ልትጠየቅ ትችላለች። ይህ ደግሞ ሆን ብሎ ፅንስ ማስወረድ ስለሚሆን ከነፍስ ግድያ ተለይቶ አይታይም።—ዘፀ. 21:22, 23፤ መዝ. 139:16