የግርጌ ማስታወሻ
b የአርኪኦሎጂ ባለሙያዎች፣ አናታቸው ላይ ቤተ መቅደሶች ያሏቸውና መወጣጫ ደረጃ የተሠራላቸው ፒራሚድ መሰል ግንቦችን በሰናዖር አቅራቢያ በቁፋሮ አግኝተዋል። የባቤልን ግንብ ለመሥራት የተነሱት ሰዎች፣ በድንጋይ ሳይሆን በጡብ እንደተጠቀሙና ለማያያዣም ቅጥራን እንዳደረጉ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል። (ዘፍጥረት 11:3, 4) ዘ ኒው ኢንሳይክሎፒዲያ ብሪታኒካ እንደሚገልጸው በሜሶጶጣሚያ ድንጋይ “እንደ ልብ ላይገኝ እንዲያውም ጨርሶ ሊጠፋ” ይችላል፤ በሌላ በኩል ግን ቅጥራን በብዛት ይገኝ ነበር።