የግርጌ ማስታወሻ g ኢየሱስ የመጨረሻዎቹን ቀኖች አስመልክቶ በተናገረው ትንቢት ላይ “የተወሰኑት የአሕዛብ ዘመናት እስኪፈጸሙ ድረስም ኢየሩሳሌም [የአምላክን አገዛዝ የምትወክለው ከተማ] በአሕዛብ ትረገጣለች” ብሎ ነበር። (ሉቃስ 21:24) ስለዚህ በኢየሱስ ዘመንም ቢሆን የአምላክ አገዛዝ ተቋርጦ ነበር፤ እንዲሁም ይህ ሁኔታ እስከ መጨረሻዎቹ ቀኖች የሚቀጥል ነበር።