የግርጌ ማስታወሻ
a ሴሬብራል ፖልዚ የተባለው በሽታ፣ በአንጎል ላይ በሚደርስ ጉዳት የተነሳ የሰውነትን እንቅስቃሴ መቆጣጠር ከባድ እንዲሆን የሚያደርጉ የጤና እክሎች የሚጠሩበት ስያሜ ነው። በተጨማሪም ይህ በሽታ የሰውነት መንዘፍዘፍ፣ የአመጋገብ ልማድ መዛባት እንዲሁም የመናገር ችግር ሊያስከትል ይችላል። ስፓስቲክ ክዎድሪፕሌጂያ የተባለው የጤና እክል ከሁሉ የከፋው የሴሬብራል ፖልዚ በሽታ ዓይነት ሲሆን እጆችና እግሮች ግትር እንዲሉ ብሎም አንገት እንዲልፈሰፈስ ሊያደርግ ይችላል።