የግርጌ ማስታወሻ a ከምሳሌው ማየት እንደሚቻለው ‘ሙሽራው እየመጣ ነው!’ (ቁጥር 6) የሚለው ጥሪ በተሰማበትና ሙሽራው በመጣበት ወይም በደረሰበት ወቅት (ቁጥር 10) መካከል ግልጽ የሆነ የጊዜ ልዩነት አለ። ንቁ የሆኑት ቅቡዓን የኢየሱስን መገኘት የሚጠቁመውን ምልክት በመጨረሻዎቹ ቀናት ሁሉ አስተውለዋል። በመሆኑም ኢየሱስ ‘እንደመጣ’ ይኸውም ንጉሣዊ ሥልጣን ይዞ እየገዛ እንደሆነ ተገንዝበዋል። ያም ቢሆን ኢየሱስ እስኪመጣ ወይም እስኪደርስ ድረስ መጽናት አለባቸው።