የግርጌ ማስታወሻ
a በዚህ ጊዜ ከተገኙት መካከል አብዛኞቹ፣ በኋላ ላይ ክርስቲያኖች እንደሆኑ ለማመን የሚያበቃ ምክንያት አለን። ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ እነሱን አስመልክቶ ሲናገር ‘ከ500 የሚበልጡ ወንድሞች’ ብሏቸዋል። አክሎም “አንዳንዶቹ በሞት ቢያንቀላፉም አብዛኞቹ ግን አሁንም ከእኛ ጋር አሉ” ማለቱ ትኩረት የሚስብ ነው። በመሆኑም ጳውሎስና በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ሌሎች ክርስቲያኖች፣ ኢየሱስ የሰጠውን ትእዛዝ በቦታው ተገኝተው ከሰሙት ወንድሞች አብዛኞቹን የሚያውቋቸው ይመስላል።