የግርጌ ማስታወሻ
b ሕዝቅኤል 37:1-14 እና ራእይ 11:7-12 በመንፈሳዊ ሁኔታ መልሶ ስለ መቋቋም ይናገራሉ፤ ይህም በ1919 ተፈጽሟል። ይሁንና የሕዝቅኤል ትንቢት የሚናገረው ሁሉም የአምላክ ሕዝቦች በጣም ረጅም ለሆነ ጊዜ በምርኮ ከቆዩ በኋላ በመንፈሳዊ መልሰው እንደሚቋቋሙ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በራእይ መጽሐፍ ላይ የሚገኘው ትንቢት፣ አመራር ላይ ያሉ ጥቂት ቅቡዓን ወንድሞችን ያቀፈ አንድ ቡድን ለተወሰነ ጊዜ እንቅስቃሴው ታግዶ ከቆየ በኋላ በመንፈሳዊ እንደሚያንሰራራ ይገልጻል።