የግርጌ ማስታወሻ
a አንድ ክርስቲያን፣ ለምግብነት የሚጠቀምባቸውን እንስሳት ለማደን ወይም ራሱን ከዱር አራዊት ጥቃት ለመከላከል ሲል እንደ ጠመንጃ ወይም ሽጉጥ ያለ የጦር መሣሪያ እንዲኖረው ሊወስን ይችላል። ይሁን እንጂ መሣሪያውን በማይጠቀምበት ጊዜ፣ ጥይቶቹን ካወጣና ምናልባትም መሣሪያውን ከፈታታው በኋላ ቢቆልፍበት የተሻለ ይሆናል። መሣሪያ መያዝ ሕጋዊ ባልሆነበት፣ የተወሰኑ ሰዎች ብቻ እንዲይዙ በሚፈቀድበት ወይም ከዚህ ጋር በተያያዘ ሌላ ዓይነት እገዳ ባለበት አገር ውስጥ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ሕጉን ይታዘዛሉ።—ሮም 13:1