የግርጌ ማስታወሻ a በአንዳንድ መጽሐፍ ቅዱሶች ውስጥ ከዮሐንስ 7:53 እስከ 8:11 ላይ የሚገኘው ሐሳብ፣ በበኩረ ጽሑፉ ላይ እንደሌለ ብዙ ሰዎች አይገነዘቡም። አንዳንዶች፣ ምንዝር መፈጸም ስህተት እንደሆነ መናገር የሚችለው ኃጢአት የሌለበት ሰው ብቻ እንደሆነ ለመግለጽ ይህን ጥቅስ እንደ ማስረጃ ያቀርባሉ። ሆኖም አምላክ ለእስራኤላውያን የሰጠው ሕግ “አንድ ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር ተኝቶ ቢገኝ ከሴትየዋ ጋር የተኛው ሰውም ሆነ ሴትየዋ ሁለቱም ይገደሉ” ይላል።—ዘዳ. 22:22