የግርጌ ማስታወሻ
f በተጨማሪም ከሐሰት ሃይማኖት ጋር ንክኪ ያላቸው የወጣቶች የመዝናኛ ክለቦችና ሌሎች የመዝናኛ ስፍራዎች አባል መሆን የለብንም። ወወክማ (የወጣት ወንዶች ክርስቲያናዊ ማኅበር) እና ወሴክማ (የወጣት ሴቶች ክርስቲያናዊ ማኅበር) የተባሉትን ማኅበራት ለዚህ እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። በአካባቢያችን ያሉት የወወክማ እና የወሴክማ ማኅበራት፣ እንቅስቃሴያቸው ከሃይማኖት ጋር የተያያዘ እንዳልሆነ ይገልጹ ይሆናል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ድርጅቶቹ ሃይማኖታዊ አመለካከቶችንና ግቦችን የሚያራምዱ ናቸው።