የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ በጥንቷ እስራኤል ነፃነት የሚታወጅበት ልዩ ዝግጅት አድርጎ ነበር። ይህ ዝግጅት ኢዮቤልዩ በመባል ይታወቃል። ክርስቲያኖች በሙሴ ሕግ ሥር ባንሆንም ከኢዮቤልዩ ዝግጅት የምናገኘው ትምህርት አለ። በጥንት ዘመን የነበረው ኢዮቤልዩ፣ ይሖዋ ለእኛ ያደረገውን ዝግጅት የሚያስታውሰን እንዴት እንደሆነ እንዲሁም ከዚህ ዝግጅት ምን ጥቅም እንደምናገኝ በዚህ ርዕስ ላይ እንመለከታለን።