የግርጌ ማስታወሻ
b የይሖዋ ስም ትክክለኛነት መረጋገጥ እንደማያስፈልገው በጽሑፎቻችን ላይ የተገለጸባቸው ጊዜያት አሉ፤ ለዚህ ምክንያት ሆኖ የቀረበው፣ ይሖዋ በዚህ ስም የመጠራት መብት ያለው ስለ መሆኑ ጥያቄ አለመነሳቱ ነው። ሆኖም በ2017 በተካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ ግንዛቤያችንን የሚያስተካክል ሐሳብ ቀርቦ ነበር። የስብሰባው ሊቀ መንበር እንዲህ ብሏል፦ “በአጭር አነጋገር የይሖዋ ስም ትክክለኛነት እንዲረጋገጥ መጸለያችን ስህተት አይደለም። ምክንያቱም ይሖዋ ያተረፈው ስም ከነቀፋ ነፃ መውጣት አለበት።”—የጥር 2018 ብሮድካስቲንግን jw.org® ላይ ተመልከት፤ ላይብረሪ > JW ብሮድካስቲንግ በሚለው ሥር ይገኛል።