የግርጌ ማስታወሻ
a ፍጹማን ባለመሆናችን ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን የሚጎዳ ነገር የምንናገርበት ወይም የምናደርግበት ጊዜ ይኖራል። እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ሲፈጠር ምን ማድረግ ይኖርብናል? ሰላም ለመፍጠር ቶሎ እርምጃ እንወስዳለን? ሳንውል ሳናድር ይቅርታ እንጠይቃለን? ወይስ ‘ቢቀየሙም ይህ የእነሱ ችግር ነው እንጂ የእኔ ችግር አይደለም’ ብለን እናስባለን? በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች በተናገሩት ወይም ባደረጉት ነገር ቶሎ መቀየም የሚቀናን ሰው ብንሆንስ? ‘እንግዲህ ይሄ ተፈጥሮዬ ነው፤ ምንም ማድረግ አልችልም’ የሚል ሰበብ እናቀርባለን? ወይስ ይህ ዓይነቱን ባሕርይ ልናስወግደው የሚገባ ድክመት እንደሆነ አድርገን እንመለከተዋለን?