የግርጌ ማስታወሻ
a ይሖዋ የጥሩ ነገሮች ሁሉ ምንጭ ነው። ለሁሉም ሰው፣ ለክፉ ሰዎች እንኳ ሳይቀር ጥሩ ነገሮችን ይሰጣል። በተለይ ግን ለታማኝ አገልጋዮቹ ጥሩ ነገሮችን ማድረግ ያስደስተዋል። ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ጥሩነቱን የሚያሳየው እንዴት እንደሆነ በዚህ ርዕስ ውስጥ እንመለከታለን። በተጨማሪም አገልግሎታቸውን የሚያሰፉ ክርስቲያኖች የይሖዋን ጥሩነት ልዩ በሆነ መንገድ የሚያጣጥሙት እንዴት እንደሆነ እንመረምራለን።