የግርጌ ማስታወሻ
a ሰዎች ለምሥራቹ ጥሩ ምላሽ ሲሰጡ እንደሰታለን፤ ጥሩ ምላሽ ሳይሰጡ ሲቀሩ ደግሞ እናዝናለን። መጽሐፍ ቅዱስን የምታስጠኑት ሰው እድገት የማያደርግ ቢሆንስ? አሊያም እስካሁን አንድም ሰው ለጥምቀት እንዲበቃ መርዳት ካልቻላችሁስ? ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ አልተሳካላችሁም ማለት ነው? በዚህ ርዕስ ውስጥ፣ ሰዎች የሚሰጡት ምላሽ ምንም ይሁን ምን በአገልግሎታችን ስኬታማ ሆነናል ሊባል የሚችለውና ደስተኛ መሆን የምንችለው ለምን እንደሆነ እንመለከታለን።