የግርጌ ማስታወሻ
a እርግጥ የእስራኤል ነገዶች እርስ በርስ የተዋጉበት ጊዜ አለ፤ ሆኖም እነዚህ የእርስ በርስ ጦርነቶች ይሖዋን አሳዝነውታል። (1 ነገ. 12:24) አንዳንድ ጊዜ ግን እንዲህ ያሉ ጦርነቶችን ይፈቅድ ነበር፤ ይህ የሆነው አንዳንዶቹ ነገዶች በእሱ ላይ በማመፃቸው ወይም ሌላ አስከፊ ኃጢአት በመፈጸማቸው የተነሳ ነው።—መሳ. 20:3-35፤ 2 ዜና 13:3-18፤ 25:14-22፤ 28:1-8