የግርጌ ማስታወሻ e ይህ ትንቢት የሚገኘው በዘካርያስ መጽሐፍ ውስጥ ቢሆንም ማቴዎስ እንዲህ ተብሎ የተነገረው “በነቢዩ ኤርምያስ” በኩል እንደሆነ ጽፏል። (ማቴዎስ 27:9) የኤርምያስ መጽሐፍ “ነቢያት” ተብሎ በሚጠራው የቅዱሳን መጻሕፍት ክፍል ላይ አንዳንድ ጊዜ መጀመሪያ ይደረግ የነበረ ይመስላል። (ሉቃስ 24:44) ማቴዎስ “ኤርምያስ” ሲል የዘካርያስን መጽሐፍ የሚያካትተውን ይህን የቅዱሳን መጻሕፍት ስብስብ በአጠቃላይ ማመልከቱ ሳይሆን አይቀርም።