“እባካችሁ እርዱኝ! ያላችሁኝ እናንተ ብቻ ናችሁ”
በሊቱዋኒያ ካዉናስ የሕክምና ዩኒቨርሲቲ የምትሠራ አንዲት ዶክተር በዚያ አገር ለሚገኘው የይሖዋ ምሥክሮች ቢሮ የጻፈችውን ደብዳቤ የደመደመችው ከላይ እንደተገለጸው በማለት ነበር። ዶክተሯ እንዲህ ብላለች:-
“በሥራ ቦታዬ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ማንበብ ጀመርኩ። ከመጽሐፉ የማገኛቸውን ሐሳቦች በአንዳንዶቹ ጽሑፎቼ ላይ ለመጠቀም አስቤ ነበር፤ ሆኖም መጽሐፉን ካስቀመጥኩበት አጣሁት። አንድ ሰው ሳይወስደው አልቀረም። ያን ያህል ውድ የሆነ ነገር ማጣቴ በጣም አበሳጨኝ። እባካችሁ ሌላ ቅጂ ላኩልኝ።
“ትምህርት ቤቶችን ስለምጎበኝና ከወጣቶች ጋር ጊዜ ስለማሳልፍ ይህ መጽሐፍ በጣም ያስፈልገኛል፤ መጽሐፉ ለብዙዎቹ ጥያቄዎቻቸው መልስ ለመስጠት ያስችለኛል። ሌላ ቅጂ ከላካችሁልኝ እቤት አስቀምጠውና በደንብ እይዘዋለሁ። ይህ መጽሐፍ በጣም ውድ የሆነ ነገር ይዟል፤ የተወሰደብኝም ለዚህ ነው። በእነዚህ አስቸጋሪ ጊዜያት ብርታት የምናገኝበት ምንጭ ያስፈልገናል። እባካችሁ እርዱኝ! ያላችሁኝ እናንተ ብቻ ናችሁ።”
ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች የተባለው መጽሐፍ በወጣቶች አእምሮ ውስጥ ለሚመላለሱ እንደሚከተሉት ላሉ ብዙ ጥያቄዎች መልስ ይሰጣል:- “ወላጆቼ ተጨማሪ ነፃነት እንዲሰጡኝ ለማድረግ የምችለው እንዴት ነው?፣” “የወላጆቼን ቤት ትቼ መውጣት ይኖርብኛልን?፣” “እውነተኛ ጓደኞች ላፈራ የምችለው እንዴት ነው?፣” “ምን ዓይነት የሥራ መስክ መምረጥ ይሻለኛል?፣” “ከጋብቻ በፊት የጾታ ግንኙነት ቢፈጸም ምናለበት?” እና “እውነተኛ ፍቅር መሆን አለመሆኑን እንዴት አውቃለሁ?” ከላይ የተገለጹት መጽሐፉ ከያዛቸው ምዕራፎች መካከል ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው። ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት ገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው በመላክ የዚህን መጽሐፍ አንድ ቅጂ ማግኘት ይችላሉ።
□ ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች የተባለውን መጽሐፍ ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።