“ይበልጥ ማወቅ አለብኝ”
ባለፈው ዓመት አንዲት ሴት እንዲህ በማለት ጽፋ ነበር:- “እንዲላክልኝ በደብዳቤ ጠይቄ የነበረው አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለው ብሮሹር ትናንትና ደረሰኝ።” ከዚህ ቀደም ብሮሹሩን የሚያስተዋውቁ ሁለት ጽሑፎች አግኝታ እንደነበር ጠቀሰች። አክላም እንዲህ አለች:- “እነዚህን ጽሑፎች ካነበብኩ በኋላ ይበልጥ ማወቅ እንዳለብኝ ስለተገነዘብኩ ብሮሹሩን የማገኝበትን ቀን በጉጉት እጠባበቅ ነበር። ብሮሹሩ እንደደረሰኝ ወዲያውኑ ማንበብ ጀመርኩ። ብሮሹራችሁ የያዘው ሐሳብ በሙሉ አሳማኝ ከመሆኑም በላይ ከመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰደ ነው።”
ስትደመድም እንዲህ ብላለች:- “ያነበብኩትን አሁኑኑ በሥራ ላይ ማዋል እንዳለብኝ ይሰማኛል።”
እርስዎም አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ባለ 32 ገጽ ብሮሹር ቢያነቡ ይጠቀማሉ ብለን እናምናለን። “ኢየሱስ ክርስቶስ ማን ነው?” ከሚለው ማራኪ ርዕሰ ትምህርት በተጨማሪ “እውነተኛው አምላክ ማን ነው?፣” “አምላክ ለምድር ያለው ዓላማ ምንድን ነው?” እና “የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?” የሚሉትን የመሰሉ ሌሎች ትምህርቶችም ያገኙበታል። እርስዎም አንድ ቅጂ ማግኘት የሚፈልጉ ከሆነ ከታች ያለውን ቅጽ ሞልተው በቅጹ ላይ ወዳለው አድራሻ ወይም በዚህ መጽሔት በገጽ 5 ላይ ከሚገኙት አድራሻዎች አመቺ ወደሆነው ይላኩ።
□ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? የተባለውን ብሮሹር ላኩልኝ።
□ መጽሐፍ ቅዱስ መማር ስለምፈልግ እባካችሁ አነጋግሩኝ።