መዝሙር 112
ይሖዋ የሰላም አምላክ ነው
በወረቀት የሚታተመው
1. አምላክ፣ ቃል ገብተሃል፤
ሰላም እንደምትሰጠን፤
መንፈስህን ’ባክህ ስጠን፤
ሰላማዊ እንድንሆን።
ልጅህ አስታረቀን
ካንተ ጋር ሰላም ሆንን፤
ወዳጆችህ እንድንሆን
መንገዱን ከፈትክልን።
2. መሪ ነው መንፈስህ፤
ይሰጣል ቃልህ ብርሃን።
በዚህ ጨለማ ዓለም ውስጥ፣
ጠባቂም፣ መሪም ሆንከን።
ሽብር ካለም ጠፍቶ፣
ጦርነት ተወግዶ
ለማየት እጅግ ብንጓጓም
እስከዚያው ስጠን ሰላም።
3. ለታማኝ ሕዝቦችህ፣
ሰላም ሰጥተሃቸዋል።
በመንፈስህ አንድ ሆነዋል፤
በኅብረት ያመልኩሃል።
መንግሥትህ በቅርቡ
ጦርነትን ያስቀራል።
ምድር ላይ ሰላም ይሰፍናል፤
ቅኖች ደስ ይላቸዋል።
(በተጨማሪም መዝ. 4:8ን፣ ፊልጵ. 4:6, 7ን እና 1 ተሰ. 5:23ን ተመልከት።)