የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 50
  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት ምን ይላል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት ምን ይላል?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • ብነቀስ ምን አለበት?
    ንቁ!—2003
  • ብነቀስ ምን ችግር አለው?
    የወጣቶች ጥያቄ
  • ከዓለም አካባቢ
    ንቁ!—2005
  • ሰውነትን በማስጌጥ ረገድ ምክንያታዊ የመሆን አስፈላጊነት
    ንቁ!—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 50

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት የሚናገረው አንድ ቦታ ላይ ብቻ ነው፤ ጥቅሱ ዘሌዋውያን 19:28 ሲሆን “በሰውነታችሁም ላይ ንቅሳት አታድርጉ” ይላል። አምላክ ይህን ትእዛዝ ለእስራኤላውያን የሰጠው፣ የአማልክቶቻቸውን ስም ወይም ምልክት በሰውነታቸው ላይ ከሚነቅሱት በአቅራቢያቸው ካሉት ብሔራት እንዲለዩ ነው። (ዘዳግም 14:2) ክርስቲያኖች ለእስራኤል ብሔር የተሰጠውን ሕግ እንዲያከብሩ ባይጠበቅባቸውም ከዚህ ሕግ በስተ ጀርባ ያለውን ሐሳብ በቁም ነገር ሊያስቡበት ይገባል።

አንድ ክርስቲያን ሰውነቱን ማስነቀስ ይችላል?

የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ስለ ጉዳዩ እንድታስብበት ሊረዱህ ይችላሉ፦

  • ‘ሴቶች በልከኝነት ራሳቸውን ያስውቡ።’ (1 ጢሞቴዎስ 2:9) በዚህ ጥቅስ ላይ ያለው ሐሳብ ለሴቶችም ሆነ ለወንዶች ይሠራል። ስለ ሌሎች ስሜት ማሰብ የሚኖርብን ከመሆኑም ሌላ አላስፈላጊ ትኩረት መሳብ አንፈልግም።

  • አንዳንዶች የሚነቀሱት በራሳቸው እንደሚመሩ ለማሳየት ሲሆን ሌሎች ደግሞ ይህን የሚያደርጉት በገዛ አካላቸው ላይ የፈለጉትን ማድረግ እንደሚችሉ ለማሳየት ነው። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ክርስቲያኖችን እንዲህ በማለት ያበረታታል፦ “ሰውነታችሁን ሕያው፣ ቅዱስና በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው መሥዋዕት አድርጋችሁ [አቅርቡ]፤ . . . ይህም የማሰብ ችሎታችሁን ተጠቅማችሁ የምታቀርቡት ቅዱስ አገልግሎት ነው።” (ሮም 12:1) መነቀስ የፈለግከው ለምን እንደሆነ ‘የማሰብ ችሎታህን’ ተጠቅመህ መርምር። መነቀስ የፈለግከው እንዲያው ሰዎች ስላደረጉት ወይም የአንድ ቡድን አባል መሆንህን ለማሳየት ብቻ ብለህ ከሆነ፣ ይህ ስሜት ጊዜያዊ፣ ንቅሳቱ ግን ዘላቂ ሊሆን እንደሚችል አትዘንጋ። መነቀስ የፈለግከው ለምን እንደሆነ ቆም ብለህ ማሰብህ ጥበብ የታከለበት ውሳኔ ለማድረግ ይረዳሃል።​—ምሳሌ 4:7

  • “የትጕህ ሰው ዕቅድ ወደ ትርፍ ያመራል፤ ችኰላም ወደ ድኽነት ያደርሳል።” (ምሳሌ 21:5) አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ለመነቀስ የሚወስኑት ‘በችኮላ’ ነው፤ ይሁንና ይህ ውሳኔያቸው ከሌሎች ጋር ባላቸው ግንኙነት ላይ ወይም ሥራ በሚፈልጉበት ወቅት ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ መዘዝ ሊኖረው ይችላል። በዚያ ላይ ደግሞ ንቅሳትን ማጥፋት ሕመም የሚያስከትል ብሎም ውድ ሊሆን ይችላል። አንዳንድ ጥናቶች እንዲሁም ንቅሳትን የሚያጠፉ ድርጅቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ፣ ሰውነታቸውን ያስነቀሱ በርካታ ሰዎች እንዲህ ማድረጋቸው ውሎ አድሮ እንደሚቆጫቸው ያሳያሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ