የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ የማመሣከሪያ ጽሑፎች—ሰኔ 2017
ከሰኔ 5-11
it-2-E 360 አን. 2-3
ሜዶናውያን፣ ሜዶን
ከፋርሳውያን ጋር ሆነው ባቢሎንን ድል አደረጉ። በስምንተኛው መቶ ዘመን ዓ.ዓ. ነቢዩ ኢሳይያስ፣ “ለብር ደንታ የሌላቸውን፣ በወርቅም ደስ የማይሰኙትን ሜዶናውያንን” ይሖዋ በባቢሎናውያን ላይ እንደሚያስነሳባቸው ትንቢት ተናግሮ ነበር። አክሎም “ቀስታቸው ወጣቶችን ይፈጃል” በማለት ተንብዮአል። (ኢሳ 13:17-19፤ 21:2) የግሪክ የታሪክ ምሁራን “ሜዶናውያን” የሚለውን ቃል፣ ሜዶናውያንንና ፋርሳውያንን በአንድነት ለማመልከት ይጠቀሙበት እንደነበረው ሁሉ ኢሳይያስም እዚህ ላይ “ሜዶናውያን” ሲል ፋርሳውያንንም ጭምር ማመልከቱ ሊሆን ይችላል። ሜዶናውያን ለብርና ለወርቅ ደንታ እንደሌላቸው መገለጹ፣ ባቢሎንን የወረሩበት ዋነኛ ምክንያት ምርኮ ማግኘት ሳይሆን ከተማዋን ድል ማድረግ መሆኑን የሚጠቁም መሆን አለበት፤ በመሆኑም በማንኛውም ዓይነት ጉቦም ሆነ ማባበያ ወይም ስጦታ ተደልለው፣ የተነሱበትን ዓላማ አይተዉም። እንደ ፋርሳውያን ሁሉ ሜዶናውያንም በዋነኝነት የሚጠቀሙበት የጦር መሣሪያ ቀስት ነበር። ሜዶናውያን ደጋኖቻቸውን አንዳንድ ጊዜ በመዳብ ወይም በነሐስ የሚለብጧቸው ቢሆንም (ከመዝ 18:34 ጋር አወዳድር) በአብዛኛው ደጋን የሚሠሩት ከእንጨት ነበር፤ ‘የባቢሎንን ወጣቶች የፈጇቸው’ በእነዚህ ደጋኖች ተጠቅመው ፍላጻዎችን በብዛት በማስወንጨፍ ሳይሆን አይቀርም፤ ፍላጻዎቹ በጠላታቸው ሰውነት ውስጥ ጠልቀው እንዲገቡ ለማድረግ ሲሉ ሹል አድርገው ይቀርጿቸው ነበር።—ኤር 51:11
ኤርምያስ፣ ባቢሎንን ከሚያጠቋት መካከል ‘የሜዶን ነገሥታት’ እንደሚገኙበት መጥቀሱ (51:11, 28) ልብ ሊባል ይገባል፤ ኤርምያስ “ነገሥታት” በማለት በብዙ ቁጥር መጠቀሙ፣ በቂሮስ ሥር ሆኖ የሚገዛ ሜዶናዊ ንጉሥ ወይም ነገሥታት እንደነበሩ የሚጠቁም ሊሆን ይችላል፤ በጥንት ዘመን ይህ መሆኑ ያልተለመደ ነገር አልነበረም። (ከኤር 25:25 ጋርም አወዳድር።) በመሆኑም የሜዶናውያን፣ የፋርሳውያን፣ የኤላማውያንና የሌሎች አጎራባች ነገዶች ጥምር ኃይል ባቢሎንን ድል ካደረጋት በኋላ “በከለዳውያን መንግሥት ላይ ንጉሥ ሆኖ የተሾመው” ዳርዮስ የተባለ ሜዶናዊ ነበር፤ ዳርዮስን የሾመው ፋርሳዊው ንጉሥ ቂሮስ መሆን አለበት።—ዳን 5:31፤ 9:1፤ “DARIUS No. 1” የሚለውን ርዕስ ተመልከት።
it-2-E 459 አን. 4
ናቦኒደስ
የናቦኒደስ ዜና መዋዕል ባቢሎን የወደቀችበትን ምሽት አስመልክቶ ሲናገር “የቂሮስ ወታደሮች ወደ ባቢሎን የገቡት ያለ ጦርነት ነው” ይላል። ይህም ኤርምያስ “የባቢሎን ተዋጊዎች መዋጋት አቁመዋል” በማለት ከተናገረው ትንቢት ጋር የሚስማማ ነው።—ኤር 51:30
it-1-E 237 አን. 1
ባቢሎን
ከዚያ ታሪካዊ ጊዜ ይኸውም ከ539 ዓ.ዓ. በኋላ ከተማዋ እየወደቀች በመሄዷ የባቢሎን ክብር መቀነስ ጀመረ። ባቢሎን፣ በፋርሳዊው ንጉሠ ነገሥት በቀዳማዊ ዳርዮስ (ሂስታስፒስ) ላይ ከአንዴም ሁለቴ ያመፀች ሲሆን በሁለተኛው ጊዜ ዳርዮስ ከተማዋን አፈራረሳት። ከተማዋ በድጋሚ በከፊል ከተሠራች በኋላም ቢሆን በቀዳማዊ ጠረክሲስ ላይ ዓምፃ ነበር፤ በዚህ ጊዜ ደግሞ ከተማዋ ተዘረፈች። ታላቁ እስክንድር ባቢሎንን ዋና ከተማው ሊያደርጋት አስቦ ነበር፤ ሆኖም በ323 ዓ.ዓ. በድንገት ሞተ። በ312 ዓ.ዓ. ናይኬተር ከተማዋን ተቆጣጠራት፤ ከዚያ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ላይ ሴሌውቅያ የተባለችውን አዲስ ዋና ከተማውን ለመገንባት ሲል በባቢሎን የነበረውን አብዛኛውን ነገር ወደዚያ አጋዘው። ያም ሆኖ ከተማዋ በክርስትና ዘመን መጀመሪያ አካባቢም የነበረች ሲሆን በዚያም የአይሁዳውያን ማኅበረሰብ ይኖር ነበር፤ ሐዋርያው ጴጥሮስ በደብዳቤው ላይ በገለጸው መሠረት ወደ ባቢሎን የሄደው ለዚህ ነው። (1ጴጥ 5:13) በባቢሎን የተገኙ በድንጋይ ላይ የተቀረጹ ጽሑፎች እንደሚጠቁሙት የባቢሎናውያን አምላክ የሆነው የቤል ቤተ መቅደስ እስከ 75 ዓ.ም. ድረስ በባቢሎን ነበረ። በአራተኛው መቶ ዘመን ከተማዋ ፈራረሰች፤ ውሎ አድሮም ሙሉ በሙሉ ጠፋች። ባቢሎን “የድንጋይ ቁልል” ሆና ቀርታለች።—ኤር 51:37
it-2-E 444 አን. 9
ተራራ
መንግሥታትን ይወክላል። ተራሮች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ መንግሥታትን ወይም አገዛዝን ለማመልከት ይሠራባቸዋል። (ዳን 2:35, 44, 45፤ ከኢሳ 41:15 እና ራእይ 17:9-11, 18 ጋር አወዳድር።) ባቢሎን ወታደራዊ ወረራ በማድረግ ሌሎች አገሮችን በማጥፋቷ “አጥፊ ተራራ” ተብላ ተጠርታለች። (ኤር 51:24, 25) ይሖዋ፣ ጦረኛ በሆኑ ሰዎች ላይ ስለሚወስደው እርምጃ የሚገልጽ አንድ መዝሙር እንዲህ ይላል፦ “አንተ ደምቀህ ታበራለህ፤ አዳኝ አራዊት ከሚኖሩባቸው ተራሮች ይልቅ ታላቅ ግርማ ተጎናጽፈሃል።” (መዝ 76:4) “አዳኝ አራዊት [የሚኖሩባቸው] ተራሮች” የሚለው አገላለጽ ጦረኛ የሆኑ መንግሥታትን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል። (ከናሆም 2:11-13 ጋር አወዳድር።) ዳዊት ስለ ይሖዋ ሲናገር “ተራራዬ ጸንቶ እንዲቆም አደረግክ” ብሏል፤ ይህን ያለው ይሖዋ መንግሥቱን ከፍ ከፍ እንዳደረገለትና እንዳጸናለት ለመግለጽ ሳይሆን አይቀርም። (መዝ 30:7 ባለማጣቀሻው አዲስ ዓለም ትርጉም፤ ከ2ሳሙ 5:12 ጋር አወዳድር።) ተራሮች መንግሥታትን ሊያመለክቱ እንደሚችሉ ማወቃችን በራእይ 8:8 ላይ “በእሳት የተቀጣጠለ ትልቅ ተራራ የሚመስል ነገር” የተባለው ምን እንደሆነ ለመረዳት ያስችለናል። እዚህ ላይ የተገለጸው ነገር በእሳት ከተቀጣጠለ ተራራ ጋር ተመሳስሏል፤ ይህም እንደ እሳት አጥፊ የሆነ አገዛዝን የሚያመለክት ሳይሆን አይቀርም።
it-2-E 882 አን. 3
ባሕር
ብዙ ሠራዊት። ኤርምያስ፣ የባቢሎን ወራሪዎች ድምፅ “እንደሚጮኽ ባሕር” እንደሆነ ገልጿል። (ኤር 50:42) በመሆኑም “ባሕሩ” ባቢሎንን እንደሚያጥለቀልቃት የተናገረው ትንቢት፣ ባቢሎንን ለመውረር የመጡትን የሜዶንና የፋርስ ወታደሮች የሚያመለክት መሆን አለበት።—ኤር 51:42፤ ከዳን 9:26 ጋር አወዳድር።
ከሰኔ 19-25
it-1-E 1214
አንጀት
የምንመገበው ምግብ ከሰውነታችን ጋር የሚዋሃደው በአንጀታችን አማካኝነት ነው። ሕዝቅኤል በተመለከተው ራእይ ላይ ጥቅልሉን እንዲበላውና አንጀቱን (በዕብራይስጥ ሜይም) እንዲሞላው የተነገረው፣ ጥቅልሉ ላይ ያለውን ነገር በአአምሮው ውስጥ ሊያብላላው እንደሚገባ በምሳሌያዊ መንገድ ለመግለጽ ነው። ሕዝቅኤል ጥቅልሉ ላይ በሰፈረው ሐሳብ ላይ ማሰላሰሉና ትምህርቱን በአእምሮው ማስቀመጡ በመንፈሳዊ ጠንካራ እንዲሆን ይረዳው ነበር። ይህም በመንፈሳዊ በሚገባ እንዲመገብና ለሌሎች የሚሰብከው መልእክት እንዲኖረው አስችሎታል።—ሕዝ 3:1-6 ባለማጣቀሻው አዲስ ዓለም ትርጉም፤ ከራእይ 10:8-10 ጋር አወዳድር።